banner

የሳውዲ መንግስት 50 ቶን ቴምር ለኢትዮጵያ በስጦታ አበረከተ።

#FastMereja I የሳውዲ መንግስት በአገሪቱ ለሚገኙ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚውል 50 ቶን ቴምር በሴቶችና ማህበራዊ ሚኒስቴር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት አስረክበዋል።

ሚኒስቴሩ ከሳውዲ መንግስት የተረከባቸው ቴምሮች የተለያዩ ለማህበራዊ ችግር ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለማገዝ እንዲውል ታስቦ እንደሆነ በዕለቱ ርክክብ ያደረጉት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ የሆኑት ክብርት ሁሪያ አሊ አስታውቀዋል ።

ሚኒስቴሩ ከተለያዩ አጋር ድርጅቶ ጋር በመተባበር ሀብት በማሰባሰብ የማህበራዊ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ተደራሽ የማድረግ ስራ እየሠራመሆኑን ገልፀዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድኤታ አቶ ምስጋኑ አረጋ በበኩላቸው የሳውዲ መንግስት ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው የሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነትንም የሚያጠናክር መሆኑን ጠቅሰዋል።

10 comments

Esu Man Leo March 18, 2025 - 9:40 am

ድርሻዬን ስጡኝ. ኣኣ.✌.??

Reply
Hayim Ril March 18, 2025 - 9:40 am

ለሙስሊም በሚለው ይስተካከልልን🙏🏿

Reply
Borsamo Boroje Borse Ware March 18, 2025 - 9:42 am

Enem ethiopiaw negnina dirshayen situgn

Reply
Oniv Brezzy March 18, 2025 - 9:42 am

እፎይ ቴምር አምሮን ነበር 👍

Reply
መቅዲ አባቴ ወድሃለሁ March 18, 2025 - 9:45 am

ዛፉን ከሆነ የሰጡን አብቹ ጫፉንም አያስነካንም🌴🌴😥

Reply
Joseph M Mengesha March 18, 2025 - 9:45 am

እነሱ ብስነስ ይሰራሉ የኛዎቹ ይጃጃሉ እንጂ😂

Reply
Ŋiġēsøn Ętĥio Mäń March 18, 2025 - 9:46 am

የዳቦ ችግር ነዉ ያለን🙄

Reply
Bekele Atakilte March 18, 2025 - 9:48 am

Tewegne bakeh

Reply
Jõhññy Dëssãlegñ March 18, 2025 - 9:48 am

በጣም ቸግሮን ነበር

Reply
ከንቱ ዓለም March 18, 2025 - 9:48 am

ስንዴ ወደ ውጭ ለምትልክ ሀገር ቴምር መርዳት ማለት የግድያ ሙከራ እንደማድረግ ነው። ስድብም ነው። ንቀትም ነው።

Reply

Leave a Comment