banner

ሴት የቢዝነስ ሥራ ፈጣሪዎች ተሸለሙ።

#FastMereja I እናት ባንክ፣ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ ኢንተርፕርነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሴቶች ጉዳይ በመተባበር ባዘጋጁት “ብሩህ እናት” የተሰኘ ሀገር አቀፍ የሴቶች የቢዝነስ ሥራ ፈጠራ ውድድር ከ1ኛ እስከ 10ኛ ደረጃ ለወጡ ሴት የፈጠራ ባለቤቶች የእውቅናና የገንዘብ ሽልማት ዛሬ መጋቢት 19/2017 ዓ.ም ጌትፋም ሆቴል በተካሄደ ስነ ስርዓት ተካሂዷል።

እናት ባንክ ከአጋር ተቋማት ጋር በመተባበር 50 የሚሆኑ ሴት የቢዝነስ ሥራ ፈጠራ ባለቤቶችን በቡት ካምፕ በማሰልጠን በሁለት ዙር የፈጠራ ሥራቸውን ለአወዳዳሪ ዳኞች እንዲያቀርቡ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል የሴቶችን የሥራ ጫና የሚያቀል የላቀና ችግር ፈች የሆነ የፈጠራ ሥራ በማቅረብ አሸናፊ ለሆኑ 10 ሴት የፈጠራ ባለቤቶች ሽልማት ተበርክቷል።

የውድድሩ አሸናፊዎች
1ኛ ሉሊት ስሙንጉስ (500ሺህ ብር ተሸላሚ)
2ኛ ቃልኪዳን ሶዴ (400ሺህ ብር ተሸላሚ)
3ኛ ማኀሌት ካሳሁን (300ሺህ ብር ተሸላሚ)
4ኛ ወይንሸት ሞገስ (200ሺህ ብር ተሸላሚ)
5ኛ ፍላጎት ተስፋዬ (150ሺ ብር ተሸላሚ)
6ኛ ሔለን ወ/መስቀል (100ሺህ ብር ተሸላሚ)
7ኛ ትዕግስት አበበ (100ሺህ ብር ተሸላሚ)
8ኛ ቅድስት በላይ (100ሺህ ብር ተሸላሚ)
9ኛ መቅደስ አድማሱ (100ሺህ ብር ተሸላሚ)
10ኛ ነፃነት ሙላት (100ሺ ብር ተሸላሚ)

#ቢዝነስ





Leave a Comment