banner

በቁጥጥር ስር ዋሉ

#FastMereja I አቶ ጽጌ ስጦታው እና አቶ ምስጢረ መዝገቡ ተብለው የሚጠሩ ግለሰቦች በቤተክርስቲያን ሥርዓተ እምነት ላይ በተለያየ ጊዜ የወንጀል ድርጊት ፈጽመዋል በሚል በቀረበባቸው አቤቱታ መሠረት ተጠርጥረው በሕግ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሕግ ባለሙያዎች ዐቢይ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡

እራሳቸውን ‹‹መሪጌታ›› ጽጌ ስጦታው እና ‹‹መሪጌታ›› ምስጢረ መዝገቡ ብለው የሚጠሩ ግለሰቦች በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓተ እምነት እና አምልኮ እንዲሁም ንዋያተ ቅድሳት ላይ በተለያዩ ጊዜያት በተደጋጋሚ በፈፀሟቸው የወንጀል ድርጊቶች በሕግ ክፍሉ በኩል በቀረበባቸው የወንጀል አቤቱታ መነሻነት የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ በዛሬው ቀን ተጠርጣሪዎችን በሕግ ቁጥጥር ሥር በማዋል የወንጀል ምርመራውን በማጣራት ላይ እንደሚገኝ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሕግ ባለሙያዎች ዐቢይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ጠበቃ አያሌው ቢታኔ ለኢኦተቤ ቴቪ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ጠበቃ አያሌው አያይዘው እንደገለጹት ከግለሰቦቹ በተጨማሪ አቶ እንዳልካቸው ዘነበ የተባለ ግለሰብ በተመሳሳይ ከዚህ ቀደም በቤተክርስቲያን ላይ ፈጽሞታል ተብሎ በተጠረጠረበት ስም ማጥፋት በቅርቡ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውሎ ቃሉን ሰጥቶ በዋስትና መለቀቁን እና በዐቃቤ ሕግ በኩልም የወንጀል ክስ አቤቱታ ተደራጅቶ ቀርቦ በሒደት ላይ እንደሚገኝ አያይዘው ገልጸዋል።

የሕግ ባለሙያዎች ዐቢይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ጠበቃ አያሌው ቢታኔ ለኢኦተቤ ቴቪ በሰጡት መረጃ ኮሚቴው ወደ ፊት ጉዳዩን ተከታትሎ የሚያሳውቅ መሆኑን ገልጸዋል።



4 comments

Teddy Getachew April 11, 2025 - 4:31 pm

Down Down Aby

Reply
Emu Teklu April 11, 2025 - 4:31 pm

ሆላ🤣

Reply
Tarik Ars April 11, 2025 - 4:32 pm

ለዛ ነው እንዳልክ የጠፋችው

Reply
Foner Ayalew April 11, 2025 - 4:32 pm

እፎይ መጡብህ

Reply

Leave a Comment