banner

አዋሽ ባንክ በመካነ ኢየሱስ ሴሚናሪዮም የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካማ ወገኖች የዓይነት እና የገንዘብ ድጋፍ

አዋሽ ባንክ በመካነ ኢየሱስ ሴሚናሪዮም የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካማ ወገኖች የዓይነት እና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

#FastMereja I አዋሽ ባንክ የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ ከተሞች ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ እያደረገ ሲሆን በዛሬው ዕለትም በመካኒሳ መካነ ኢየሱስ ሴሚናሪዮም በመገኘት ለአቅመ ደካማ ወገኖች የዓይነት እና የገንዘብ ድጋፍ መርሃ-ግብር አካሄዷል።

አዋሽ ባንክ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ላለፉት 30 ዓመታት በርካታ ማህበረሰብ ተኮር ስራዎችን በመስራት በተለያዩ ጊዜያት በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎች ዘርፈ ብዙ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል፤እያደረገም ይገኛል፡

አዋሽ ባንክ ታላላቅ ህዝባዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላትን ምክንያት በማድረግ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ አቅመ ደካማ ወገኖች ዘርፈ ብዙ ድጋፎችን እያደረገ ሲሆን የ2017 የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ አዲስ አበባን ጨምሮ በመላው ሃገራችን ከአንድ መቶ በላይ በሚሆኑ የድጋፍ መስጫ ጣቢያዎች ከአስር ሺህ በላይ ለሚሆኑ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ፣ጧሪ ለሌላቸው አረጋውያን እና ሌሎች ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ከ63 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለበዓሉ የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል።

ከዚህም ባሻገር በመንግስትና በማህበረሰቡ የሚከናወኑ የልማት ስራዎችን በመደገፍ ረገድ ባንኩ የበኩልን አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በተያያዘም ባንኩ የ1446ኛውን የረመዳን ወርን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ ከተሞች ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ለሙስሊም ወገኖች ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ተመሳሳይ ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል፡፡





Leave a Comment