#FastMereja I ዕለቱ ጥር 2 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11:30 በሚሆንበት ግዜ በድሬዳዋ ከተማ ወረዳ 6 በልዩ ቦታው ፈረስ መጋላ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የግድያ ወንጀል መፈፀሙን ከፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።
የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በወንጀል ምርመራ ዘርፍ የሰው መግደል እና ልዩ ልዩ ወንጀሎች ምርመራ ዲቪዥን ኃላፊ ኢ/ር ተመስገን ተሰማ ለድሬ ፖሊስ ሚዲያ እንደገለጹት ተከሳሽ ሳሙኤል ኃይሌ ተፈራ ከዛሬ 29 ዓመት በፊት ከባለቤቱ ጋር በሟች ቤተሰብ የመኖሪያ ግቢ ውስጥ ተከራይቶ በጉርብትና አብረው ይኖሩ እንደነበር ተናግረው ታዲያ በአንዲት ቀን ተከሳሽ ሳሙኤል ኃይሌ ሟች ግለሰብ ባለቤቴን አማግጦብኛል የሚል ጥርጣሬን በማሳደሩ በመካከላቸው የነበረው ሰላም በመደፍረሱ ለመለያየት ይገደዳሉ ።
ኢ/ር ተመስገን ተሰማ አክለው እንደገለፁት ተከሳሽ ሳሙኤል ኃይሌ በውስጡ ከፍተኛ ቂም ይዞ ሟች በማያቅበት ሁኔታ ለመግደል ቢያስብም ምቹ ግዜ እና ሁኔታ አልፈቅድ ብሎት 29 አመታት ይቆጠራሉ።
ታዲያ ከዚህ ሁሉ አመታት በኋላ ተከሳሽ ሳሙኤል የህብረት ባንክ ጥበቃ ስራ ተቀጥሮ በሚሰራበት ወቅት ለጥበቃ የታጠቀውን ክላሽንኮፕ የጦር መሳሪያ ከ 30 ፍሬ ጥይት ጋር ይዞ መደበኛ ስራውን በመስራት ላይ ሳለ በዛው አካባቢ በሹፍርና ስራ የተሰማራው ሟች ውሀ ለመግዛት ወደ ሱቅ በሚሄድበት ግዜ ተመልክቶት ለ29 ዓመታት ያቄመውን ቂም ለመወጣት የታጠቀውን መሳሪያ እንደምቹ ሁኔታ በመጠቀም ሟች ግለሰብን በአንድ ጥይት ጀርባውን መትቶ መሬት ከጣለው በኋላ በተኛበት ደጋግሞ ጭንቅላቱን እና የተለያዩ የሰውነት ክፍሉን በጥይት በመምታት የግድያ ወንጀሉን ከፈጸመ በኃላ ለማምለጥ ሲሞክር የቀጠናው ፖሊስ አባላት ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉን ኢ/ር ተመስገን ተሰማ ተናግረዋል ።
በዚህም ጉዳዩን ለማጣራት የተዋቀረው የምርመራ ቡድን ጉዳዩን አጣርቶ በፍትህ ሚንስቴር ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የመሰረተውን የክስ መዝገብ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከ2016 ዓ.ም እስከ 2017 ዓ.ም ድረስ የክስ መዝገቡን ሲመረምር ቆይቶ መጋቢት 23 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ሳሙኤል ኃይሌ ተፈራን በቀረበበት የሰው እና የሰነድ ማስረጃ ጥፋተኛ ሆኖ በማግኘቱ በ16 ዓመት እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል።
#ችሎት

8 comments
ቂመኛ
29 አመት ቡሃላ 😂
የገደለው በእስራት is not fair
የኔ ጎረቤቴ ይሔን ዜና ቢሰማ ምን ሊል ነው🙄
እሁድ ሊያገባ ቅዳሜ ያማገጠበትን ይበቀል ወይ😭
29 አመት አቤት ክፋት እደግመዋለሁ 29 አመት ———–
29 አመት ወጥሮ ቢሰራ 11 ሚስት ማሰለፍ ይችል ነበር 😁
በአመክሮ 10 ዓመት ከ8 ወር ተቀልቦ አምሮበት ይወጣል የሞተ ተጎዳ
Firidu bezabetisa yemiwodatini misti amagixo yigebowal