#FastMereja I አንድ በምስረታ ላይ ያሉ ድርጅት ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት በዓለም ለመጀመርያ ጊዜ የሚካሄደው የወንድ ልጅ የዘር ፍሬ / ስፐርም እሽቅድድም የፊታችን ኤፕሪል 25 ማለትም ከአራት ቀናት በኃላ በሎስ አንጀለስ ሆሊውድ እንደሚካሄድ አስታውቋል።
የስፐርም እሽቅድድሙ የሚያዘጋጀው ድርጅት በወጣት ሚልየነሮች የተመሰረተ ሲሆን በውድድሩም የደቡብ ካሊፎርንያ ዩኒቨርሲቲና በሎስ አንጀለስ የሚገኘው የካሊፎርንያ ዩኒቨርስቲ የሚሳተፉበት የስፐርም ዋና ውድድር ይሆናል ተብሏል።
ውድድሩ በማይክሮስኮፒክ ካሜራ ስር የሚደረግ ሲሆን ሙሉ ሂደቱም እንደሚቀረፅ ተነግሯል። እንደ አዘጋጆቹ ገለፃ ከሆነም ውድድሩ ሶስት ምዕራፎች ይኖሩታል የተባለ ሲሆን በእግር ኳስ ጨዋታ ጊዜ ብሎም በተለያዩ ሰፖርታዊ ክንውኖች ወቅት እንዲደረገው በኮሜንታተሮች የታገዘ የውድድር ትንተና ይሰጥበታልም ተብሏል።
ከአዘጋጆቹ አንዱና የድርጅቱ መስራች የሆነው ኤሪክ ዙህ የሰፐርም ውድድሩ እንዲሁ ዝም ብሎ ተራ ውድድር አይደለም ያለ ሲሆን የኛ እቅድ ጤናን ወደ ውድድር ማምጣት ነው ብሏል። አክሎም በወንዶች የዘር ፍሬ / ስፐርም ጤና ዙርያ ብዙም አይወራም ነገር ግን ሊወራለት የሚገባ ራሱን የቻለ ትልቅ ርእስ ነው እኛም እሱን ለማድረግ ነው እየጣርን ያለነው ሲል ተደምጧል።
Via: ዳጉ ጆርናል
https://t.me/fastmereja
https://t.me/fastmereja

10 comments
የተበላሸ ዓለም
ስንት ሺ ነው ውድድሩ🤣🤣🤣🤣
ኧረ እኔ አለው አወዳድሩኝ😊
መዳውስ ዳኛውስ ፣ ኪኪክክክ ዘንድሮ የማንሰማው ምን ቀረ!
ከንቱ ዓለም 😭
እኔንም መዝግቡኝ
😳😳😳
በሩጫ ነው ወይስ… በምንድነው?
ሸልማቱ ስንት ነው?😎😆
ወይ ጉድ 😄