banner

የፕሮቴስታንት የእግር ኳስ ውድድር ሊካሄድ ነው

#FastMereja I “ግሬስ ቶርናመንት” የተሰኘው ይህ ውድድር በግሬስ ክርስቲያን ሚዲያ መዘጋጀቱ ዛሬ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።

“ግሬስ ቶርናመንት” ማህበረሰባችን ለስፖርት ለማንቃት እና እርስ በእርስ ተቀራርቦ ስፖርታዊ ባህልን እንዲያዳብር ለማስለመድ የተዘጋጀ የእግር ኳስ ውድድር እንደሆነ ተነግሯል።

በዚህ የእግር ኳስ ውድድር 16 ቡድኖች የሚሳተፉ ሲሆን፣ በሰላምና በፍቅር ለወንጌል ምሳሌነት በሚሆን መልኩ፣ እርስ በእርስ ውድድራችን እናደርጋለን ተብሏል።

ይህ ውድድር የፊታችን ቅዳሜ የክብር እንግዶች የቤተክርስቲያን መሪዎችና አገልጋዮች በተገኙበት ግንቦት 9/2017 ከ9:00 ጀምሮ በቡልቡላ ሜዳ ላይ የሚከናወን ሲሆን፣ የመክፈቻ ጨዋታው በናዝራውያን ቡድንና፣ በዘጸአት ቤተ ክርስቲያን ቡድኖች መሐል በሚደረገው ጨዋታ እንደሚጀመር ተገልጿል።





1 comment

ማህደር የሽወንድ May 15, 2025 - 4:06 pm

ወንጌሉን ጨርሰው ነው🙄

Reply

Leave a Comment