banner

ዩቲዩብ ላይ በርካታ ድንቅ ስራዎች ቲፎዞ ባለማግኘታቸው ሳይደመጡ ተጭነው ተቀምጧል። ዛሬ ከሶስት አመት በፊት የጫነ አንድ ድንቅ

ዩቲዩብ ላይ በርካታ ድንቅ ስራዎች ቲፎዞ ባለማግኘታቸው ሳይደመጡ ተጭነው ተቀምጧል። ዛሬ ከሶስት አመት በፊት የጫነ አንድ ድንቅ የሙዚቃ ስራን አድምጠን ለጆሯችን ድንቅን ስራን አሰምተን አጨብጭበን ይህማ ለህዝብ ይነገር ብለን ይዘን መጥተናል።

ስለዚህ ስራ ብዙ ማውራት ብዙ መፃፍ አንፈልግም አድምጡት ስራው ይናገራል። ግጥሙ፣ ዜማው፣ ቅንብሩ፣ ድምፃዊው አብሮ የተወለዱ ነው የሚመስሉት።

የሙዚቃው መጠሪያ እራሱ ድንቅ ነው “እያዳነ ያማል” የሚሰኝ ሲሆን ኢሳያስ ታምራት ተጫውቶታል። የግጥሙን የተወሰነ ስንኝ እናካፍላችሁ ቀሪውን ዩቲዩብ ላይ ተመልከቱት።

***

በምን ተረታው አልልም፣ ቁም ነገርሽ ይለያል
እንዲህም ያለ ፍቅር፣ ለካ እንደዚህ ያማል
ያማል እያዳነ ያማል እያዳነ ያማል

እንደ እናት አንጀት እንስፍስፍ፣ የደግነት ሙዳይ
ውለታን አይቆጥርም፣ የአንቺ መውደድ ጉዳይ
ሳቅሽ ቀኝሽ ግራን አያይ፣ ከምድር ነሽ ከሰማይ

ዛሬ ሳሳው ለነፍሴ፣ አስታርቀሽኝ ከራሴ
…

ድምፃዊ ኢሳያስ ታምራት (እያዳነ ያማል)
ግጥም: አልፍአገድ እምሻው
ዜማ: አህመድ ተሾመ (ዲንቢ)
ቅንብር: አብርሃም ኪዳኔ

#FastMereja
#ሾውቢዝ

Leave a Comment