#FastMereja I በአሜሪካን ሐገር የሚገኘው ኢትዮጵያን ኮሚኒቲ ዲቪሎፕመንት ካውንስል የተባለው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የተመሰረተበትን 42ኛ ዓመት ምስረታ በዓል አስመልክቶ ባሳለፍነው ሀሙስ አርሊንግተን ፣ ቨርጂኒያ በሚገኘው ሬኔሳንስ ሆቴል ታዋቂ ግለሰቦች ፣ የማህበረሰብ አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ዝግጅት ላይ ስደተኞችን ያገለገሉ፣ ማህበረሰባችንን ያገዙ እና ለሰላም እና ለፍትህ የቆሙ ሦስት ግለሰቦችን በደመቀ ስነ ስርዓት የዕውቅና ሽልማት ሰጥቷል።
ድምጻዊ ታሪኩ ካንጋሲ ለሰላም እና ለፍትህ መስፈን ላበረከተው ላቅ ያለ አስተዋፅዖ ሊሸለም ይገባዋል ብሎ ድርጅቱ በመወሰኑ በአሜሪካን ሐገር በእንግድነት ተገኝቶ በዝግጅቱ ላይ የተዘጋጀለትን ሽልማት እንዲቀበል አስፈላጊውን መስፈርት አሟልቶ አዲስ አበባ ለሚገኘው የአሜሪካን ኤንባሲ የግብዣ የጥሪ ወረቀት ልኮለት ነበር።
ድምጻዊ ታሪኩ ካንጋሲም ቪዛ ለመውሰድ ቃለ መጠይቅ ለማድረግ በኤንባሲው በቀጠሮው ቀን ከተገኘ በኋላ ፣ በቪዛ ኦፊሰሩ ቃለ መጠይቅ ተደርጎለት ነበር። ኦፊሰሩ አማረኛ መናገር የሚችል ፈረንጅ ነበር፣ ታሪኩንም በአማረኛ “ለምንድን ነው ወደ አሜሪካን ሀገር የምትሔደው?” ብሎ ሲጠይቀው ፣ ታሪኩ “አሜሪካን ሐገር በቋሚነት ለመኖር” ብሎ ይመልስለታል ፣ የቪዛ ኦፊሰሩም ወደ ሀገርህ የማትመለስ ስለመሰለኝ ብሎ ቪዛውን ይከለክለዋል።
ፈረንጁ የቪዛ ኦፊሰርና ታሪኩ አማርኛ ቋንቋ ሁለተኛ ቋንቋቸው ስለሆነ፤ ጠያቂውና ተጠያቂው ሳይግባቡ ታሪኩም ወደ አሜሪካ ሳይመጣ ቀርቷል።
በዚህም ምክንያት ታሪኩ በሌለበት በወኪሉ አማካኝነት ሽልማቱ ተበርክቶለታል። ከሽልማቱ በኋላ በቪዲዮ ተቀድቶ በስፍራው ከጂንካ ባስተላለፈው መልዕክት “ይህንን ሽልማት ስለ ሸለማችሁኝ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ፣ ወደ አሜሪካን ሀገር ለመምጣት አስቤ አልተሳካም፣ አሁን ጂንካ ተመልሼ በግብርና ስራዬ ላይ ተሰማርቻለሁ “ ብሏል:: የግብርና ስራዉን እየሰራ ባስተላለፈው የቪዲዮ መልዕክት።
በዚህ ዝግጅት ላይ በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንየተባበሩት መንግስታት ድርጅት አምባሳደር የነበሩት ሊንዳ ቶማስ እና የነጩ ቤተመንግስት የሰደተኞች ጉዳይ አማካሪ የነበሩት ማርሌላ ኢስኮባሪ ተገኝተዋል።
በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ የቪዛ ክፍል ኦፊሰር ሆነው የሚላኩ ዲፕሎማቶች ፣ ወደ አዲስ አበባ ከመላካቸው በፊት በአሜሪካን ሀገር የአማርኛ ቋንቋ እንዲያጠኑ እየተደረገ ስለሆነ የአማርኛ አስተርጓሚ አያስፈልጋቸውም ፣ በአሁኑ ወቅትበኤንባሲው ውስጥ ከሚሰሩ የቪዛ ኦፊሰሮች መካከል ቢያንስ ሦስቱ አማርኛ ቋንቋን አቀላጥፈው ይናገራሉ።
በድምጻዊ ታሪኩ ካንጋሲ የተቀነቀነው ዲሺታ ጊና ወይንም አዳም ወንድሜ የተሰኘው ነጠላ ዜማ በዩቲዩብ ከተለቀቀ ጊዜ ጀምሮ ከ38 ሚሊዮን በላይ ተመልካች አግኝቷል።
ድምጻዊ ታሪኩ ጋንካሲ የሚኖረው ጂንካ ሲሆን በግብርና ስራ ይተዳደራል። በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባል በመሆንም በውትድርና አገልግሎ የሚያውቀው ታሪኩ ከዚህ በፊት “እምዬ ጂንካ” ሲል የተጫወተው ሙዚቃ አለው።
በትውልድ ሴኔጋላዊ በዜግነት አሜሪካዊ የሆነው ዝነኛው ሙዚቀኛ ኤኮን ዲሺታ ጊናን ሪሚክስ አድርጎ ተጫውቶታል።
መረጃው የመዝናኛ መረጃ ገጽ ነው።
#ኪነ_ጥበብ
#ሾውቢዝ
