0
#FastMereja I በአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በአስራ አንዱም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ደንብ 557/2016 መነሻ ባደረገ ጥብቅ ቁጥጥር በሚያዚያ ወር ብቻ 9,617 እግረኞች መቅጣቱን አስታወቀ።
ባለፈው ሚያዚያ ወር በአስራአንዱም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እግረኞች ትክክለኛውን የመንገድ አጠቃቀም እንዲከተሉ ተከታታይነት ባለው የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር በተጓዳኝ በተካሄደ ቁጥጥር የእግረኛ ማቋረጫ /ዜብራ/ ላይ ያልተሻገሩ፣ በተሸከርካሪ መንገድ ላይ የተጓዙ፤ ተሸከርካሪን ከፊት እያዩ ባላተጓዙና በሌሎችም ጥፋት የተገኙ እግረኞች በገንዘብ ተቀጥተዋል፡፡
ከገንዘቡም ውጪ በማህበራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ የተደረጉ እግረኞች መኖራቸውንና ይኸው በግንዛቤ የተደገፈ የእግረኛ ቁጥጥር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል፡፡

8 comments
የዛሬው ዜና ደሞ fast ያበደ ነው 🔥🔥🔥🔥
ብርቅ አይደለም እቤት እየመጡ እየቀጡን ነው😭
በሚኪና እየሄድኩ መብራት ጥሰሀል ተብዬ ተከሰስኩ ወርጄ እሱን ልከፍል በእግሬ እየሄድኩ በዜብራ አላቃረጥክም ተብዬ ተከሰስኩ እሺ በምን እንሂድ።
ጥሩ አፈፃፀም ነው በርቱ
ቆይ ነብስም የመንግስት ነው እንዴ?
Daniel Gebremeskel
እንደዛ ከሆነ ሁላችንም ጌታ ረድቶን ነው ገብተን እየወጣን ያለው።9ሺ?
በሆነው ባልሆነው አስቃዩት ይሄን ህዝብ ከድንዛዜው የነቃ ቀን ግን ትችለዋለህ