0
#FastMereja I የተወዳጁ ድምፃዊ ጥላሁን ገሰሰ ስድስት ሙዚቃዎች በአዲስ መልክ ሊሰሩ ነው። የጥላሁንን ዘፈኖች በድጋሚ የሚጫወታቸው ድምፃዊ ኢሳይያስ ታምራት መሆኑን አውቀናል።
ኢሳያስ በባላገሩ አይዶል የሙዚቃ ውድድር ላይ ዳዊት ፅጌን ተከትሎ ሁለተኛ ደረጃን ያገኘ እንደነበር ይታወቃል።
በድጋሚ የሚሰሩት የጥላሁን ዘፈኖች የ13 ወር ፀጋ፣ እቱ ገላ፣ እንባዬ ቦይ ይስራ፣ ከረምናታ፣ አልቻልኩም እና አንድ የኦሮሚኛ ሙዚቃ ሲሆኑ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ወደ አድማጭ ይደርሳሉ ተብሏል።
የእነዚህ ሙዚቃዎች ፕሮዲየሰር ሽርጉድ ኢንተርቴይመንት ሲሆን ድርጅቱ በቅርቡ በሚሌኒየም አዳራሽ ኤፍሬም ታምሩ፣ ጎሳዬ ተስፋያ፣ አለማየሁ ሂርጶ እና ሜላት ቀለመወርቅ የዘፈኑበትን የሙዚቃ ኮንሰርት አሰናድቶ የነበረ ነው።
በድጋሚ የሚሰሩት የጥላሁን ሥራዎች በሽርጉድ ኢንተርቴይመንት የዩቲዩብ ቻናል ላይ የሚለቀቁ እንደሆነም አውቀናል።
ድርጅቱ ለሙዚቃዎቹ ድርሰት ባለቤቶች ህጋዊ በሆነ መንገድ ክፍያዎችን ፈፅሞ የድጋሚ መስራት መብት ማግኘቱን ለኢትዮጲካሊንክ አስታውቋል።
#ኪነ_ጥበብ

7 comments
Min silehonu edisat ayasfeligewum
ደስ የሚል ዜና ነው ኢሱ ትልቅ አቅም ያለው ሰው ነው በዚህ ይምጣልን!
ነብሱ በገነት በሰላም እንድታርፍ አልፈለጉም ማለት ነው ??
ፈቅጃለሁ ኣንተ ከሆንክ 👍
Ehem tibeb nw
ይሄ ልጅ ያጣው ጥሩ ማንጀር ነው። እንዴት ተነግሮ የማያልቅ አቅም እያለው አሁንም ዘፈን ይገርባል!
ይገርማል አጋጣሚ የጥላሁንን ሙዚቃወች እያዳመጥሁ ነው ይሄን ፖስት ማነበው እና ሙዚቃወቹ አይሰለቹኝም ❤❤❤