banner

7 ቢራ የሞንድ ሴሌክሽን ወርቅ ጥራት ተሸላሚ ሆነ

#FastMereja I በዩናይትድ ቤቨሬጅ የሚመረተው ኢትዮጵያዊው 7 ቢራ የ2025 የሞንድ ሴሌክሽን የወርቅ ጥራት ተሸላሚ መሆኑን ዛሬ ሰኔ 7/2017 ዓ.ም የስራ ኃላፊዎቹ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።

ይህ ሽልማት አለምአቀፋዊ እውቅናን ያገኘንበት እንዲሁም የስራችንን ወጤት ያየንበት በመሆኑ ከሜዳሊያም በላይ ነው ብሏል።

ይህ ስኬት ከተጠቃሚዎች እምነት ባሻገር ዩናይትድ ቢቬሬጅ አክሲዮን ማህበር በዓለም አቀፍም ሆነ በሀገር ውስጥ ያለውን ገበያ ያጠናክራል በተጨማሪም ለአዳዲስ ስራዎች ፤ ተደራሽነቶች ፤ አጋርነቶች እንዲሁም ስኬቶች መንገድ ይከፍታል ተብሏል።

ዩናይትድ ቤቨሬጅ የሚያመርታቸው አንበሳ ቢራ እና 7 ቢራ ሲሆን ሰቨን ቢራ ይኽን ሽልማት ማሸነፉ ዩናይትድ ቤቬሬጅ ለተዓማኒነቱ እና ለምርት ጥራቱ ተግቶ እንደሚሰራ ማረጋገጫ እንደሆነ በመግለጫው ላይ ተገልጿል።





1 comment

Antish Man June 14, 2025 - 1:26 pm

እኔ ስማር ደብተር ተሸልሜ አውቃለሁ😂😂

Reply

Leave a Comment