banner

የአፍሪካ ህፃናት ቀን በስለእናት የበጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥ ተከበረ

#FastMereja I በየአመቱ ሰኔ 9 የሚከበረው የአፍሪካ ህፃናት ቀን በደቡብ አፍሪካ የሶዌቶ ከተማ ውስጥ የተፈጠረውን አስከፊ ሀዘን ለማሰብ ሲሆን በዛ ዕለት በሺዎች የሚቆጠሩ በጥቁር ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ህፃናት የተጎዱበት እና የሞቱበት ወቅት ነበር፡፡

ስለእናት ለችግር የተጋለጡ እና የተጎዱ ህጻናትን እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውን ለመታደግ የተቋቋመ ድርጅት ሲሆን በተለያዩ የህጻናት ክብካቤ አማራጮች ላይ ይሰራል።

ስለእናት የበጎ አድራጎት ድርጅት ላለፉት 23 ዓመታት በተለያዩ የሀገሪቱ ከልሎች እና አሁን ላይ ደግሞ በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ሻሸመኔ ከተማ ላይ ላሉ ወላጆቻቸውን በተለያዩ ምክንያት ላጡ ህጻናት እና አቅመ ደካማ ቤተሰቦች እየደገፈ ይገኛል።

በተጨማሪም ስለእናት የድርጅቱን መለያ አርማ እና የማህበራዊ ትስስር ገፆችን ማሻሻያ አድርጓል።

የአርማ ለውጥ ለማድረግ ያስፈለገበት ዋና ምክንያት ድርጅቱ የሚያከናውናቸውን ፕሮግራሞች የሚወከል እንዲሆን ከማሰብ እና ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ የአሰራር ሂደት ለመከተል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው ተብሏል።





Leave a Comment