#FastMereja I በአሁኑ ሰአት ብዙዎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ካለማድረጋቸው የተነሳ ተላላፊ ለሆኑና ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች ችግር ሰለባ እየሆኑ መጥተዋል የተባለ ሲሆን ይህንንም ችግር ለመቅረፍ በቀላሉ በቤትዎ እና በስፖርት ቤቶች ሆነው ሊሰሩ የሚችሉበት ፊት አውራሪ የተሰኘ የስፖርት አፕ ስራውን ጀምሯል፡፡
ዛሬ ሰኔ 11/2017 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ “በእውቀት ላይ ያልተመሰረተ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያይላል፡፡” የተባለ ሲሆን ፊትአዉራሪ ፊትነስ ሁሉም ማህበረሰብ ክፍል ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ የበኩሉን እየተወጣ ያለ ድርጅት ሲሆን በስፓርቱ ዘርፍ የራሱን አሻራ አስቀምጦ ከኢትዮጵያ አልፎ በሁሉም የአለም ሃገሮች ላይ በመዘዋወር ስፓርቱን ከፍ ማድረግ ዋነኛ አላማዉ ነዉ ተብሏል።
ፊት አዉራሪ አፕሊኬሽን ሁሉም በስልኩ በማውረድ ያለ ዳታ በኦፍላይን ባሉበት ሆነው ስፖርታዊ እንቅስቃሴን መስራት እንደሚቻል ተገልጿል።
ፊት አውራሪ ፊትነስ የተመሰረተዉ በ2016 ዓ.ም ሲሆን “ፊት አዉራሪ” ማለት ቀዳሚ ወይም መሪ ማለት ነዉ :: ተቋሙ በስፓርቱ ዘርፍ ከፊት ሆኖ አዳዲስ ነገሮችን ለመፍጠር ከፍተኛ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ተነግሯል።
#ስፖርት




