#FastMereja I እንረዳዳ የአረጋውያን በጎ አድራጎት ማህበር በእጁ የያዛቸውን አረጋውያኖች እንዲሁም የአረጋውያን የልጅ ልጆች በተሻለ መልኩ ድጋፍ ለማድረግ ወደ ህዝቡ አድርሶ ማስተዋወቅና ገቢ ማሰባሰብን ዓላማው ያደረገ “ለአረጋውያን እሮጣለሁ፣ የድርሻዬን እወጣለሁ” በሚል መሪ ቃል መነሻና መድረሻው አድዋ መታሰቢያ ሙዚየም የሆነ የጎዳና ላይ ሩጫ ሰኔ 15/2017 ዓ.ም ማዘጋጀቱን ዛሬ በሳፋየር አዲስ ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።
h3000 – 5000 ሰው ይታደምበታል ተብሎ የሚጠበቀው በዚሀ 5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በአትሌቶች መካከል የሚደረግ ውድድር የሚኖር ሲሆን በዕለቱም የአ.አ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮች፣ የአ.አ ወጣቶችና ስፖርት ሃላፊዎች፣ የኢትዮጲያ አረጋውያን ጡረተኞችማህበር አባላት፣ የማህበሩ አማባሰደሮች፣ አርቲስቶች፣ ታዋቂ አትሌቶችና አሰልጣኖች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በቦታው ይገኛሉ ተብሏል።
የመሮጫው ቲሸርት ዋጋው ለአዋቂ 500 ብር ለታዳጊዎች በ400 ብር ለሽያጭ ቀርቧል፡፡
እንረዳዳ የአረጋውያን በጎ አድራጎት ማህበር የአረጋውያንን መሰረታዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻቸውን ለመፍታት እንደ እድሜ ባለፀግነታቸውም የተከበሩና ጤናማ እንዲሆኑ በማለት 1990 ዓ.ም የተቋቋመ ደርጅት ነው፡፡
ማሀበሩ ከተቋቋመ ጀምሮ ለ824 አረጋዊያን በተለያዩ መንገድ ድጋፍ እያደረገ ሲሆን ከእነርሱም በተጨማሪ 1558 የልጅ ልጆቻቸውን በተዘዋዋሪ ተጠቃሚነት ምዝገባ በማድረግ እያደረገም ይገኛል፡፡




