0
#FastMereja I በጋምቤላ ክልል አኙዋሃ ብሔረሰብ ዞን አቦቦ ወረዳ ውስጥ የተከለከለ የአልኮል መጠጥ ይዘው በሚዘዋወሩ ግለሰቦች ላይ ፖሊስ ባደረገው ጥብቅ ክትትል 190 የጂን አልኮል መጠጦችን በቁጥጥር ሥር አውሎ እንዲወገዱ ማድረጉን የወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
የአቦቦ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ አቶ አሮፖ ኡበንግ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ፣ ሕገ-ወጥ የአልኮል መጠጦችን በሚያዘዋውሩ ግለሰቦች ላይ ወረዳው ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርግና አስፈላጊውን ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጸዋል።
አክለውም የተከለከሉ የአልኮል መጠጦች በማኅበረሰቡ ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ በመሆናቸው፣ ኅብረተሰቡ ይህንን ሕገ-ወጥ ተግባር የሚያከናውኑ ግለሰቦች ሲያጋጥሙት በአፋጣኝ ለወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ጥቆማ በመስጠት ትብብር እንዲያደርግ አዛዡ ጥሪ አቅርበዋል።

4 comments
ወይ ፈብሪካዉን መዝጋት ከድሀ ላይ ከምትደፉ የተረገመች ሀገር
እኔ መጠጣት ባቆምኩበት ወቅት በመሆኑ ነው እንጅ በጣም ያናድዳል
ብሄራዊ አረቄ ፋብሪካ እኮ የመንግስት ነው እንዴት ቢዳፈሩ ነው መንግስት ያመረተውን ምርት የሚደፉት
Zemua Buna 😭