banner

በዘሪሁን ግርማ የተዘጋጀው «ሚድያ እና የኢትዮጵያ ቤተክስርቲያን» መጽሐፍ ኅዳር 27 ሊመረቅ መሆኑ ተገለጸ

#FastMereja I ለዓመታት በሚዲያ ዘርፍ ሲሰራ የቆየው ዘሪሁን ግርማ ያዘጋጀው «ሚድያ እና የኢትዮጵያ ቤተክስርቲያን» የተሰኘ ሁለተኛ መጽሐፍ በቅርቡ ለንባብ እንደሚበቃ፣ በፍሬንድሺፕ ኢንተርናሽናል ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገለጸ።

ቀደም ሲል «የዘር ሐሳቦች» የተሰኘ መጽሐፍን ለአንባቢያን ያበረከተው ደራሲው፣ በዚህ አዲስ መጽሐፉ የኢትዮጵያ ክርስቲያናዊ ሚዲያ አጀማመርን፣ እድገትንና በተለያዩ ወቅቶች ያሳለፋቸውን ለውጦች እንደሚዳስስ በመግለጫው ተጠቁሟል። ከታሪኩ ጀርባ ያሉ ክስተቶችን በማስቃኘትም፣ የሚዲያ ተጽዕኖ በቤተክርስቲያንና በማኅበረሰብ ላይ ምን እንደሚመስል ይተነትናል።

መጽሐፉ ኃላፊነት የሚሰማው የሚዲያ አጠቃቀም ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ፣ የሚዲያ ተደራሽነት እየሰፋ በመጣበት ወቅት መልእክቶች በሙያዊ ሥነ ምግባር መቅረብ እንዳለባቸውና የዘርፉ ባለሙያዎች ያለባቸውን ሕጋዊ ኃላፊነት እንደሚያመላክት ተገልጿል። እንዲሁም ሚዲያ በኃላፊነት ሲመራ የሚያስገኘውን በጎ ፋይዳ እና ኃላፊነት በጎደለው መንገድ ሲጠቀሙበት ሊከሰት የሚችለውን ጉዳት ለውይይት እንደሚያቀርብ ተነግሯል።

«ሚድያ እና የኢትዮጵያ ቤተክስርቲያን» መጽሐፍ ኅዳር 27 ቀን 2019 ዓ.ም. በኢንተርናሽናል ኢቫንጀሊካል ቤተክርስቲያን በይፋ የሚመረቅ ሲሆን፣ የመሸጫ ዋጋውም 700 ብር መሆኑ ተገልጿል።





Leave a Comment