0
#FastMereja I ኢትዮጲያ የራሷን ጋዝ ለማምረት ጥረት ስታደርግ መቆየቷ የተገለፀ ሲሆን በመጪው መስከረም የ 2018 ዓ/ም አዲስ አመት ላይ ወደ ገበያ ሊቀርብ መሆኑን ሰምተናል፡፡
ይህ የተሰማው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) በሀገሪቱ ከሚገኙ የሚዲያ አመራሮች እና የኮሚኒኬሽን ባለሙያዎች ጋር በዛሬው ዕለት እያደረጉት ባለው የጋራ ውይይት ላይ ነው፡፡
በዚህ መድረክ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጲያ ማዳበሪያን ከዳንጎቴ ግሩፕ ጋር ለማምረት ከስምምነት ላይ መድረሷንም አስታውቀዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ውጥን መያዙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የመንግስትን የ2017 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸምን በተመለከተ ለምክር ቤት አባላት ባቀረቡበት ወቅት መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡
በወቅቱም የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታው ከ2.5 እስከ 3 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚጠይቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረው ነበር፡፡
በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጪው የ 2018 መስከረም ወር ታላቁ የህዳሴ ግድብ ተጠናቆ ሪቫኑ እንደሚቆረጥ በዚሁ መድረክ ላይ አንስተዋል፡፡
ዘገባው የኢትዮ ኤፍ ኤም ነው

10 comments
ጋዝ ሀሀሀሀሀሀሀ የጋዛ ሰርፅ ሊዘጋ ነው😂😂😂
ሰክሶ አደር የሆነ ሰው😂
በለው ውሸት😂
አቤት ሳክስ 😘😘😘
በምላሱ ነው?🤔
አውርቶ አደር
በወሬ እኮ እስካሁን ከቻይና ቀጥለን ከዓለም 4ተኛ ሁነን ነበር😋😏
ኢራን ጉድ ሆነች በሉኛ 😂😂😂
አይመቸህ
የሃበሻ ተርት ስገጥም ጋዝ ጋዝ የምል ዜና ይሉታል ይሄ ነው