0
#FastMereja I ፊንቴክ ኢንቨስትመንት ኃ/የተ/የግል ማህበር ለ250 ደንበኞች የኤሌክትሪክ የቢዋይዲ መኪኖችን ዛሬ ሰኔ 17/2017 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ በተከናወነ ዝግጅት ለደንበኞች አስረከበ!
ይህ መርሐ ግብር 20 ሺህ ኤሌክትሪክ መኪኖችን የመገጣጠም እና የማቅረብ ፕሮጀክት አካል እንደሆነ ነው የተገለጸው።
ፊንቴክ ኢንቨስትመንት በየ120 ኪሎ ሜትሩ የኤሌክትሪክ ቻርጅ ማድረጊያ መሙያ ጣቢያዎችን ለመገንባት ማቀዱ በዝግጅት ስነስርዓቱ ላይ ተብራርቷል።
ፊንቴክ ኢንቨስትመንት ከቢዋይዲ ኩባንያ “Ocean Network” የኤለክትሪክ መኪኖችን ገዝቶ ከ950 ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ በ5 ዓመት የሚከፈል ከወለድ ነፃ የ50% (የሃምሳ ከመቶ) የብድር አገልግሎት አዘጋጅቶ ከ8 ዓመት ዋስትና ጋር በማቅረብ እንቅስቃሴ ላይ የነበረ ሲሆን ድርጅቱ ቀደም ሲል በኦሮሚያ ባህል ማእከል፣ በስካይ ላይት ሆቴል እና በወዳጅነት ፓርክ እስከ 250 የኤለክትሪክ መኪኖች ለደንበኞች አስረክቧል ተብሏል።
ፊንቴክ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ማቅረቡ ኢትዮጵያ ለምትከተለው አረንጓዴ ኢኮኖሚ አጋዥ ይሆናል ተብሏል።





2 comments
Mensur ምን ይሰራል
እነ መንሱር የገቡበት ጤነኛ አይሆንም ያው ለናንተ ብለን ዜናውን የላምበረት ብለን ጀምረነዋል ….አፋችን እስከሚያብሱልን ድረስ 😛