banner

ወጣት አማረ አዲስ የአዩቴ ኢትዮጵያ 2025 ውድድርን አሸነፈ።

#FastMereja I የወጣቶች የግብርና እና ቴክኖሎጂ ውድድር ዛሬ ሰኔ 18/2017 በኃይሌ ግራንድ ሆቴል ፍጻሜውን አግኝቷል።

የሀይፈን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ ቴዎድሮስ አየለ ባደረገው ንግግር ርሃብንና ድህነትን ለማጥፋት በግብርናዉ ዘርፍ ያሉ ሥራ ፈጣሪዎችን ማበረታታትና ማብቃት አስፈላጊ ነው ብሏል።

ግብርናን የሚያዘምን የቴክኖሎጂ ውድድር የሆነው አዩቴ አፍሪካ ቻሌንጅ ኢትዮጵያ 2025 ከገንዘብ ሽልማት በተጨማሪ የፈጠራ ሃሳባቸው ወደ መሬት ወርዶ በስራ ላይ እንዲውል ድጋፍ ይደረግላቸዋል ተብሏል።

በውድድሩ ከ1 እስከ 10 የወጡ ተወዳዳሪዎች እውቅና የተሰጣቸው ሲሆን ከአንድ እስከ አምስት ለወጡት የገንዘብ ሽልማት ተብርክቷል።

የውድድሩ አሸናፊዎች
1ኛ አማረ አዲስ 15ሺህ የአሜሪካን ዶላር ተሸልሟል
2ኛ ዶክተር በአምላክ ካሳሁን 10ሺህ የአሜሪካን ዶላር ተሸልሟል
3ኛ ማህደር ሰለሞን 7ሺህ የአሜሪካን ዶላር ተሸልማለች
4ኛ ሁንዱማ አቶምሳ 5ሺህ የአሜሪካን ዶላር ተሸልሟል
5ኛ ቤተልሄም ጥላሁን እና ጀቤሳ ጫላ 2,500 የአሜሪካን ዶላር ተሸልሟል





Leave a Comment