#FastMereja I ሁለገብ ኦንላይን ሶሉሽን ዛሬ ሰኔ 28/2017 በፍሬንድሺፕ ፓርክ የ”ሁሉ ስፖርት ፌስቲቫል” ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል።
የዘንድሮውን ክረምት ምክንያት በማድረግ ስፖርቱ መነቀቃት ያግዛል ያለውን የ”ሁሉ ስፖርት ፌስቲቫል’ን እንዲሁም የተለያዩ የስፖርት ሁነቶችን ለማከናወን ከፍተኛ በጀት መመደቡን አሰታውቋል፤ ይህ የክረምት የስፖርት ፕሮጀክት በተለያዩ ክልል ከተሞች በተለያዩ የስፖርት አይነቶች የሚከናወን ስለመሆኑም የሁለገብ ኦንላይን ሶሉሽን ዋና ሰራ አስከያጅ አቶ ክብሮም ገብረመስቀል ገልፀዋል።
በዛሬው እለትም ሁለገብ ኦንላይን ሶሉሽን በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የተዘጋጀውን መተግበሪያ ይፋ ተደርጓል ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ልዩ የሁለገብ ቤተሰብ የሆኑ ተሳታፊዎች ከኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በተሰጠው ፍቃደ መሰረት:-
📌 አቶ ለአለም ገብረኪዳን ገብረ መስቀል የBYD SEAGULL ኤሌክትሪክ መኪና ከመቐለ ተሸልሟል።
📌 አቶ ይብራህ ፈተዊ የኤሌክትሪክ ሳይክል ከአደዋ ተሸልሟል።
📌 አቶ ጫላ ኦላኒ የስማርት ስልክ ከጋምቤላ ተሸልሟል።
📌 አቶ አማኑኤል እዮብ ፕሌይ ስቴሽን ከሃላባ ቁሊቶ ተሸልሟል።
📌 አቶ ምናየው ንጉሴ ከአርባ ምንጭ የስማርት ቴሌቪዥን ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ድርጅቱ ማህበራዊ ሃላፊነት በመወጣት ረገድ በበርካታ በጎ ስራዎች ላይ ንቁ ተሳታፊ ነን ያሉት የደርጀቱ ሽያጭ ክፍል ሀላፊ አቶ ፍፁም ተሾመ በየአመቱ 5 በመቶውን የተጣራ የድርጅቱን ትርፍ ትርጉም ላለው የማህበረሰብ ተነሳሽነት እንሰጣለን ሲሉሞ ገልፀዋል።
ሁሉ ስፖርት ፌስቲቫል ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 5 ድረሰ የሚከናወን ይሆናል።




