0
#FastMereja I በአዲስ አበባ ከተማ ከ68 ሺህ በላይ ደንብ ተላላፊ እግረኞች መቀጣታቸውን የከተማዋ የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታወቀ።
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ከበበው ሚዴቅሳ በእግረኞች የመንገድ አጠቃቀም ላይ በተደረገ ቁጥጥር 68 ሺህ 640 ደንብ ተላላፊ እግረኞች መቀጣታቸውን ተናግረዋል።
ከነዚህም መካከል 30 ሺህ 616 የሚሆኑት በገንዘብ እንዲሁም 37 ሺህ 790 እግረኞች ደግሞ የአገልግሎት ስራ እንዲሰሩ መደረጋቸውን ጠቁመዋል።
ቅጣቱ የተላለፈው ዜብራ ጠብቀው የማይሻገሩ፣ አደባባይ የሚያቋርጡ፣ እንዲሁም የትራፊክ መብራት በማያከብሩ እግረኞች ላይ መሆኑን አመልክተዋል።
አክለውም ከ80 በመቶ በላይ የትራፊክ አደጋ ተጎጂ እግረኞች መሆናቸውን ገልጸው፤ ይህንን ለመከላከል የእግረኛ መንገድ ማሻሻል ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም እግረኞች የትራፊክ ደህንነት ህጎችን በማክበር በተሽከርካሪ ከሚደርስ አደጋ ብሎም ሞት እራሳቸውን እንዲጠብቁ ማሳሰባቸውን የዘገበው ኢፕድ ነው።
