banner

በአዲስ አበባ የተመረጡ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ስራ ጀመሩ

#FastMereja I የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳርደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በተመረጡ የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት ላይ መደበኛ የስራ ቀናት ማራዘሙን ገለጸ።

ነዋሪዎች በሙሉ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 እና እሁድ ከቀኑ 6፡30 ድረስ ማንኛውንም አገልግሎት ከማዕከል መስሪያ ቤቶች ጀምሮ ክ/ከተማ እና ወረዳዎች ላይ አገልግሎት ማግኘት የሚቻል መሆኑን ገልጿል።

በተጠቀሱት ቀናት አገልግሎት የሚሰጡ ከማዕከል – ወረዳ ያሉ ተቋማት
📌 ንግድ ቢሮ፣
📌 ገቢዎች ቢሮ፣
📌 መሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ፣
📌 መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ፣
📌 ግንባታ ፍቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን፣
📌 ህብረት ስራ እና የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ እና ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ላይ በተጠቀሰው መሰረት አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን አስታውቋል።

Leave a Comment