banner

የኢትዮጵያውያን ስፖርት እና ባህል ፌዴሬሽን በአውሮፓ 20ኛ አመቱን በጀርመን ፍራንክፈርት ሊያከብር ነው።

#FastMereja I የኢትዮጵያውያን ስፖርት እና ባህል ፌዴሬሽን በአውሮፓ ከመጪው ሐምሌ 22 እሰከ ሐምሌ 26/2017 ዓ.ም 20ኛ አመት የምስረታ በአሉን በጀርመን እንደሚያከብር ዛሬ በአዲስ አበባ በተሰጠ መግለጫ ተነግሯል።

ከሰላሳ በማያንሱ ክለቦች መካከል ከሚደረጉ የእግር ኳስ ውድድሮች ባሻገር የሃገር ባህልን የሚያንፀባርቁ የሙዚቃ ድግሶች እንደሚኖሩ ተገልጿል።

እንዲሁም 10 የሚያህሉ የሀገራችን ትላልቅ አርቲስቶች የሙዚቃ ዝግጅታቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።

የኢትዮጵያ ስፖርት እና ባህል ፌዴሬሽን በ2025 ፍራንከፈርት ለሚካሄደው ፌስቲቫል ከኪንግሶሎ ፕሮሞሽን፣ ጋር በዚህ ዘርፍ በጋራ ለመስራት መስማማቱ ተገልጿል።





1 comment

Nati Man July 18, 2025 - 4:10 pm

ብስራት ሱራፌል

Reply

Leave a Comment