banner

ከ40 በላይ ዲዛይን ያላቸው ሁለተኛው የወንበር ኤግዚቢሽን እየተካሔደ ነው።

#FastMereja I ሁለተኛው የወንበር ኤግዚቢሽን በገርጂ ቢ ኤም ኤ ህንፃ የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተከፍቷል።

በደብሻ የቤት ውስጥ ዲዛይን ድርጅት አማካኝነት ለ2 ቀን በሚካሄደው በኢትዮጵያ ሁለተኛው የወንበር ኤግዚቢሽን በገርጂ ቢ ኤም ኤ ህንፃ የተከፈተ ሲሆን ይህ ኤግዚቢሽን በወንበር ስራ ላይ ተሰማርተው ለሚገኙ ሰዎች አዳዲስ የስራ ፈጠራዎችን ለመሳየት እንደሚረዳ የደብሻ የቤት ውስጥ ዲዛይን ድርጅት መስራች የሆኑት አቶ ብሩክ ደበበ በመክፈቻውለት ገልፀዋል።

እንደ አቶ ብሩክ ገለፃ የዚህ ኤግዚቢሽን አላማዎች አዳዲስ በወንበር ዲዛይን ስራ ላይ ለማምጣትና ድግግሞሽ የሆነ ዲዛይንን በማስቀረት እንዲሁም እድሉን ሳያገኙ ቀርተው በዘርፉ ላልተሰማሩ ሰዎች የስራ እድልና የስራ ግንኙነት እንዲኖራቸው ማድረግ ነው

በወንበር ኤግዚቢሽን በዘርፉ ላይ ያሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችም ተሳትፈዋል።

የዚህ የወንበር ኤግዚቢሽን የተካሄደው አዘጋጁ ደበሻ የቤት ውስጥ ዲዛይን 8ኛ አመቱን በማክበር ላይ ስለሆነ እሱንም ታሳቢ ለማድረግ ነው ተብሏል

8 አመት ከተመሰረተ የሞላው ደብሻ የቤት ውስጥ ዲዛይን የተለያዩ የቤት ውስጥ ዲዛይን ስራዎችን በመስራት ላይ የሚገኝተቋም ነው



Leave a Comment