0
#FastMereja I በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አሪ ዞን ደቡብ ኣሪ ወረዳ በደረሰ የመሬት ናዳ የ5 ሰዎች ህይወት በማለፉ የጋሞ ዞን መንግስት የተሰማውን ሀዘን ገለፀ። በክልሉ ኣሪ ዞን በደቡብ ኣሪ ወረዳ በኮመር ቀበሌ ሞልሽር ልማት ቡድን በቀን 13/11/2017 ዓ.ም በትላንትው እለት በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ከምሽቱ 2:30 ላይ በደረሰው ናዳ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፍ ችሏል።
በተከሰተዉ ናዳ ምክንያት የአንድ ቤተሰብ ሙሉ የቤተሰብ አካል ህይወት ያለፈ ሲሆን ከህጻናትን ጨምሮ 3 ወንድ 2 ሴት በአጠቃላይ የ5 ሰዎች ህይወት ማለፍ ችሏል።
ከዚህም በተጨማሪ 3 መኖርያ ቤቶች ከቤት እንስሳት ጋር በናዳው መስጠሙ ታውቋል ።
በቦታው የመንግስት አካላት፣ ቀይመስቀል እንዲሁም የአከባቢው ነዋሪዎች ደርሰው ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ።
ወቅቱ ክረምት በመሆኑ በሌሎች የክልሉ አከባቢዎችም ተመሳሳይ የሆነ አደጋ እንዳይከሰት የስጋት ቦታዎች ጋ ቅድመ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ።
የዞኑ መንግስትም በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች መፅናናትን ይመኛል።




6 comments
rip
Hiikooti ??
በጣም ያሳዝናል እንደ እኛ እንደ ከንቾ እንዳይሆን ሰዎች ወደ ናዳው እንዳይጠጉ ጥንቃቄ ይደረግ
ያሳዝናል ።
የፈጣሪ ያለህ በጣም ያሳዝናል 😥
Rip ,may God comfort all Family members 😭😭