0
#FastMereja I አድማስ ዩኒቨርሲቲ በአዲስ አበባ ከተማ በድህረ ምረቃ፣ በዲግሪና በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና መርሀ ግብር ያስተማራቸውን ከ 6,000 በላይ ተማሪዎች ዛረረ ሐምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ አስመርቋል።
ዩኒቨርሲቲው ላለፋት 26 ዓመታት በመደበኛና በርቀት ትምህርት፣ በድግሪ፣ በዲፕሎማና በሰርተፊኬት በርካታ ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን በዛሬዋ ዕለትም ከ6,000 በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል ከእነዚህ ውስጥ ከ71 ፐርሰንቱ በላይ ሴቶች እንደሆኑ ተገልጿል።
በምረቃ መረኃ ግብሩም ከተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የሜዳሊያና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ የዋንጫ ሽልማት ተበርክቷል።




