0
#FastMereja I “ኮር ፊትነስ ስፖርት ኃ/የተ/የግ/ማኀበር” ቤተሰባዊነት የሚያጠናክር ዓመታዊ የስፖርት ቤተሰብ ፕሮግራም የሚያዘጋጅ ሲሆን የዘንድሮውን መርሃ ግብር ዛሬ ሐምሌ 27/2017 ዓ.ም አካሂዷል።
የኮር ፊትነስ ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ ትርንጎ ጤናው (ናኒ) ባደረጉት ንግግር በ2015 ዓ.ም የተመሰረተው ኮር ፊትነስ ስፖርት በተመሠረተ በአጭር ጊዜ ውስጥ በምንሰጠው ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት፣ አብዛኛው ደንበኞቻችን ጤናማና አምራች ዜጋ እንዲሆኑ ሰርቷል ብሏል።
ወንድማማችነትንና ቤተሰባዊ ትስስርን በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተወጣ የሚገኝ የስፖርት ማዕከል መሆኑን ገልጿል።
ኮር ፊትነስ የህብረተሰብ ጤና ላይ ነው የሚሰራው፣ ታሞ ሃኪም ቤት ከመሄድ በፊት በስፖርት በሽታን መከላከል እንደሚቻል እያሳየ ያለ ድርጅት መሆኑ ተነግሯል።




