0
#FastMereja I በአዲስ አበባ በተለያዩ ስፍራዎች የንግድ ማዕከላትን እየገነባ የሚገኘው ካቮድ ኮሜርሺያል ዛሬ ነሀሴ 02/2017 ዓ.ም ከላክስ አዲስ ፕሮፐርቲስ ጋር የስጦታ ሞል ብቸኛ የሽያጭ ወኪል በማድረግ ስምምነት ፈጽሟል።
18 ሺሕ ካሬ ሜትር አጠቃላይ ሥፋት የያዘውና በ18 ወራት ግንባታው እንደሚጠናቀቅ በተነገረው ስጦታ ሞል የተለያዩ የስጦታ ግብዓቶችና ተዛማጅ አገልግሎቶች በአንድ ጣሪያ የያዘ ግዙፍ ሞል መሆኑ ተነግሯል።
ካቮድ ኮሜርሺያል የሚገነባው ስጦታ ሞል ብቸኛ የሽያጭ ወኪል ላክስ አዲስ ፕሮፐርቲስ ኃላፊዎች በስካይ ላይ ሆቴል ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና ሚዲያዎች በተገኙበት የፊርማ ሥነ ሥርዐት አካሔደዋል፡፡
#ቢዝነስ


