banner

በርካታ ወጣቶችን ስራ የሚያስጀምረው ፕሮጀክት በአምቦ ከተማ ይፋ ሆነ

#FastMereja I ጤግሮስ ትሬዲንግ እና ሊንክ አስ ትሬዲንግ ቻይና ከሚገኘው ኢዩ ሸገር ድርጅት ጋር በመሆን “ብርሀን ገበያ” የተሰኘ ወጣቶችን የመስሪያ ሱቅ ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ዛሬ ነሀሴ 02/2017 ዓ.ም በአምቦ ከተማ አስጀመረ።

ዛሬ በአምቦ ከተማ ይፋ የሆነው ፕሮጀክት ከአምቦ ከተማ አስተዳደር እና ከኦሮሚያ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር ሲሆን በመጀመሪያ ዙር ለ20 ወጣቶች የሱቅ ርክክብ ተደርጓል።

በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የአምቦ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሃጫሉ ገመቹን ጨምሮ የኦሮሚያ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ከድር እንዳልካቸው እና ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ ባለስልጣናት እና እንግዶች ተገኝተዋል::

ሱቆቹ የተሟላ እቃዎችን በማስገባት ስራ እንዲጀምሩ የተደረገ ሲሆን ያለምንም ማስያዣ ለአምስት አመታት ሰርተው ወደ ቀጣይ ከፍ ያለ ደረጃ ለማድረስ እንደታሰበ ተነግሯል።

በ5 ዓመት ጊዜ ውስጥ የተሻለ አፈፃፅም ላሳዩ የመኪና ሽልማት እንደሚበረከት ተገልጿል። በዚህ ፕሮጀክት ከአምቦ በተጨማሪ በበርካታ የሀገሪቱ ክፍሎች ወጣቶችን ያለ ምንም ማስያዣ ስራ የማስጀመሩ ፕሮጀክት እንደሙቀጥል በመድረኩ ላይ ተነግሯል።





Leave a Comment