0
#FastMereja I አርቲስት ሸዋፈራው ደሳለኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞችን ይቅርታ ጠየቀ። አርቲስት ሸዋፈራው በሰይፉ ሾው ላይ ቀርቦ ይቅርታ መጠየቁን ፋስት መረጃ ተመልክቷል። አሁን የማምንበትን መፅሐፍ ቅዱስ የሰጠችኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ናት፣ እኔ ብሽሽቅ ውስጥ አልገባም፣ ወንጌል ብሽሽቅ አይደለም፣ “እዛ ሰፈር” እያልኩ ለነበረው ስብከት ይቅርታ እጠይቃለሁ። ሌላው አለ የተባለውን እኔ አላልኩም ማስረጃ መቅረብ አይቻልም። እዛ ሰፈር ላልኩት ይቅርታ እጠይቃለሁ ብሏል።

10 comments
ኧረ ቀስስስስ ይጨርስ 😳
አሁን ደሞ ለ እንጀራው እንጂ አልተጸጸተም ብለን እንወግረዋለን😂ዶላር ሊበላ😂
በቃ የሞተ ሰው ነው ለእኔ🙄
ግድ ይላል 💪
አርቲስቶች እና ፖለቲከኞች ለጉድ ፈነጩባት ይቺን ሀገር
ፈጣሪን የሚፈሩ የሚመስሉ፤ ነገር ግን ፈጣሪን ሳይቀር ከሚያስፈሩ ሰዎች እንጠንቀቅ 🙆🏻♂️🙆🏻♂️😔😔
” ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ። ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብን የሚወዱ፥ #ትምክህተኞች፥ #ትዕቢተኞች፥ #ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥ ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ #መልካም የሆነውን #የማይወዱ፥ ከዳተኞች፥ #ችኩሎች፥ #በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤ #የአምልኮ መልክ አላቸው #ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ። 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡1-5
የግንባር ፓክ አወጣኮ ገርጥቶ😳 ሙንድል ሙንድል ሲልኮ ኩስስ ሚል አይመስልም😁😂
እስቲ ማል ደፋር ወጥ ቀማሽ ነገር ነህ😂😂😂
ደሞ አላለም ያሉትስ መች ሊጠይቁን ነዉ ለማንኛዉም እማይነካ አትንኩ።
እኔኮ የሚገርመኝ ግን ክርስቶስን የሚከተል ክርስቲያን ነኝ የሚል ክርስቶስ ፍቅርን እንድንሰብክ እንጂ ስድብና ብሽሽቅ እንድናስተምር አይመክርም ዘሎ የሰውን እምነት ያውም ክርስቶስን ጠንቅቃ የምታውቅና የምታመልክ የኦርቶዶክስን እምነት በዚህ ደረጃ ለማብጠልጠል መሞከር ነውርም ሀጥያትም ነው ያውም 1 ጥቅስ ጠቅሶ ታውቆ ተሙቶ🤔