#FastMereja I ወጣት መብቱ አዱኛ ይባላል ገርጂ ታክሲ ተራ ለረጅም አመት ሊስትሮ ነበር የሚሰራው ጫማዎችን ሶሎችን በመቀየር ከቆዳ ጋር በደንብ ተዋወቀ፣ የእኔ ጥንካሬ ችግሬ ነው የሚለው መብቱ በ7 አመቴ ነው ስራ መስራት የጀመርኩት ይላል።
በሊስትሮ ብቻ ህይወቴን ማቆየት የለብኝም በማለት መንግስት በሰጠኝ ሼድ የቆዳ ጫማዎችን መስራት ጀመርኩ ከዛም አልፎ የሌዘር ጃኬቶች፣ ሸሚዞች፣ ቦርሳዎች በማምረት የሌዘር ምርት እንደጀመረ ይናገራል።
ረጅም ጊዜ ማስረከብ ውስጥ ነበር የቆየነው አሁን ሶሻል ሚዲያ ላይ በተለይ ቲክቶክ ላይ ስራዎቻችንን እያስተዋወቅን ስንመጣ ገበያ አግኝተናል Her leather የተሰኘ የመሸጫ ሱቅ በገርጂ እና በካዛንቺስ በመክፈት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ገልጾልናል።
ከሊስትሮ የተነሳው ወጣት መብቱ በአሁኑ ወቅት በኄር ሌዘር ስር ለ20 ዜጎችን ቀጥሮ እያሰራ የሚገኝ ሲሆን ምርቶቹም ከጥራት በተጨማሪ ባለሞያ የተጨነቀባቸው ከዘመኑ ጋር የሚሄዱ ዲዛይኖች እንደሆኑ ይናገራል።
በተለይ የውጭ ሀገር ዜጎች የኄር ሌዘር ምርቶችን በስፋት እንደሚጠቀሙ የሚናገረው መብቱ ምርቶቻችን ኤክስፖርት ስታንዳርድ መሆናቸው ኩራት ይሰማኛል ብሏል።
በስራው ላይ እንደተግዳሮት የገጠመኝ የአቅም ውስንነት የፋይናንስ እጥረት ነው፣ የፋይናንስ ተቋማት እንደዚህ አይነት ማደግ የሚችሉ አነስተኛ ድርጅቶችን ማበደር ቢችሉ ስራዎቻችን በማስፋፋት የዓለም አቀፉን ገበያ ተቀላቅለን በጥራት መወዳደር እንደሚቻል ይናገራል።
ሁለት ቅርጫፎችን ከፍቶ እየሰራ የሚገኘው Herr leather ቁጥር አንድ ገርጅ ሮባ ዱባይ ሞል አንደኛ ፎቅ፣ ቁጥር ሁለት ካሳንቺስ ኢሌሌ ሆቴል ፊት ለፊት ይገኛል።
ምርቶቹን ለመግዛት ገበያ ትስስር ለመፍጠር ስልክ
0960161330
0944031330
በሶሻል ሚዲያ
Herr leather ብለው ያገኙታል።
#ቢዝነስ





1 comment
ጀጋኑ 💪