#FastMereja I የኦሮሞ ምርምር ማኅበር ጥልቅ ጥናት ከተደረገባቸው በኃላ የበርካታ የኦሮሞ ምሁራን ተሳትፎ ያደረጉበትን አራት የተለያዩ መጽሐፍቶች በሦስት ቋንቋንዎች አሳትሞ ሊያስመርቅ መሆኑን በዛሬዉ እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አሳዉቋል።
በ14 ምሁራንና የታሪክ አጥኚዎች ስብስብና በኦሮሚያ ጥናት እና ምርምር ማህበር አማካኝነት የተዘጋጀው “ፊንፊኔ ዛሬ እና ነገ ” ጨምሮ 4 መጽሐፎች የፊታችን እሁድ በኢሊሊ ሆቴል ሊያስመርቅ መሆኑ ተገልጿል።
ለንባብ የሚበቁት መፅሀፍት 1. Finfinnee Past and Present, (English, Afan Oromoo, Amharic)
2. A Partially Annotated Bibliography of Oromoo
3. In search of Knowledge: some Issues and Perspective on Oromo studies
4. The Gada system of Governance (Seera Caffee Oromoo)
አቶ ታቦር ዋሚ የማህበሩ የቀድሞ ሰብሳቢ ሲሆኑ ማህበሩ የተቋቋመበት ዋና ዓላማዉ የኦሮሞን ታሪክ በመፅሀፍት በሚገባ ለማሳወቅ እና ለአጥኚዎች፣ ለታሪክ ተመራማሪዎችና ለሚዲያ ባለሞያዎች እንደ ማጣቀሻና ግብአት እንዲሆን ታስቦ እንደሆነ ነው የተናገሩት።
አያይዘውም የኦሮሞ ህዝብ አብዛኛው ታሪክ የተፃፉት በሃገሬው ሰው ቋንቋ እና ባህሉን በሚያውቀው ሳይሆን በሌላ ሃገር ሚሽነሪዎች እና ከውጭ ሃገር በመጡ ታሪክ ፀሃፊያን እነሱ በፈለጉትና በዘፈቀደ የተጻፈ በመሆኑ ትክክለኛውን ታሪክና መጠቀስ የሚገባው አልተጠቀም ነው ያሉት።





1 comment
ለ4መጽሐፍ አስራ አራት አህያ መድከም ነበረበት ወይ