banner

በ3 ሚሊዮን ብር የተሰራው “መድረሻዬ” ፊልም ለእይታ ሊበቃ ነው

#FastMereja I በሬድ ኤክስ ፊልም ፕሮዳክሽን ተዘጋጅቶ በንጉሱ ፊልም ፕሮዳክሽን የቀረበዉ መድረሻዬ የተሰኘው ፊልም የፊታችን ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም በአለም ሲኒማ ተመርቆ ለእይታ እንደሚበቃ በዛሬ ዕለት በቱሊኘ ኦሎምፒያ ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተነግሯል።

ፊልሙ ከዘጠኝ ወራት ያላነሰ ጊዜ ወስዷል ያሉት አቶ ንጉሱ መልጌታ ልዩ ልዩ ወጪዎችን ሳይጨምር ከ3 ሚሊየን ብር ያላነሰ ወጪ ፊልሙ ላይ ውሏል ብለዋል።

ፊልሙ በርካታ ታዋቂ የሚባሉ የሲኒማ ባለሙያዎች የተሳተፉበት በዓይነቱ ለየት ያለ ድንቅ ሀሳብና ታሪክ ይዞ የመጣ የተባለለት ሲሆን ሰለሞን ሙሄ ፣ መኮንን ላዕከ፣ ዘላለም ይታገሱ ፣ንጉሱ መልጌታ፣ ፍቅረተ ደሳለኝ፣ ህይወት ጌታሁን፣ ሰለሞን ተካ፣ ችሮታው ከልካይ እና ሌሎች አንጋፍና ወጣት ተዋንያን ተሳትፈውበታል። በተጨማሪ ከዋና ካራክተሮች ውጪ በአጠቃላይ ከ70 ያላነሱ ተዋናዮች ተሳትፈውበታል ተብሏል።

ከዚህ ቀደም በንጉስ ፊልም ፕሮዳክሽን ሆነ በሬድ ኤክስ ፒክቸርስ የስራናቸዉ ፊልሞች ደረጃቸውን የጠበቁ እና በተለያዩ የሽልማት ዘርፎች ማሸነፍ የቻሉ ናቸው።በንጉሱ ፊልም ፕሮዳክሽን የተሰሩት 4 ፊልሞች ሲሆኑ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው እና በሀገሪቷ የሲኒማ ሽልማት ላይ እውቅና ያገኙ ሲሆን በሬድ ኤክስ ፒክቸርስ የተሰሩትም ቢሆኑ ከኢትዮጵያ አልፈው በውጭ ሀገራት የፈልም ፌስቲቫሎች ላይ የቀረቡና ጥሩ ደረጃ የተሰጣቸው ናቸው።





Leave a Comment