#FastMereja I ኦሮሚያ ባንክ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኳንተም ቴክኖሎጂ አ.ማ ሚልኪ ዲጂታል የብድር አገልግሎትን በመጠቀም በአሁን ይብረሩ፤ በኋላ ይክፈሉ (Fly Now, Pay Later) መርኃ-ግብር አብሮ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ኦሮሚያ ባንክ ከሁለቱ ተቋማት ጋር በጋራ ከተስማማባቸዉ ጉዳዮች አንዱ፤ ባንኩ በቅርቡ ስራ ላይ ያዋለዉን ሚልኪ ዲጂታል የብድር አገልግሎት መተግበሪያ በመጠቀም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደንበኞች ገንዘብ ቢያጥራቸዉ ያለምንም ማስያዣያ እና ዋስትና በሚልኪ ተበድረዉ የበረራ ቲኬት በመቁረጥ ከበረሩ እና ጉዳያቸዉን ከፈፀሙ በኋላ ተረጋግተዉ የሚከፍሉበት አይነተኛ አማራጭ አመቻችቷል፡፡
“አሁን ይብረሩ፤ በኋላ ይክፈሉ” የተሰኘው መርኃ-ግብር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደንበኞች ጊዜያዊ የገንዘብ እጥረት ሳያሳስባቸዉ ሚልኪ መተግበሪያን በመጠቀም የአየር ቲኬታቸዉን በመቁረጥ ሀገር አቀፍም ሆነ አለም አቀፍ በረራዎችን ካከናወኑ እና ጉዳያቸዉን ከፈፀሙ በኋላ ስራቸዉን እየሰሩ እንዲከፍሉ እድል ይፈጥርላቸዋል፡፡
የሶስቱ ተቋማት እስትራቴጂካዊ አጋርነት የጥሬ ገንዝብ ዝዉዉርን በመቀነስ የሀገራችንን ዲጂታላይዜሽን ጉዞ ከማዘመን እና የፋይናንስ አካታችነትን ከመደገፍ በተጨማሪ የዜጎችን ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ በእጅጉ ያሳልጣል ተብሎ እንደሚታመን ተነግሯል።
#ቢዝነስ




