#FastMereja I የቅጥራን ማኑፋክቸሪንግ ሜዲካል ኢኪዩፕመንት ትሬዲንግ ፒኤልሲ ስራ ማስጀመሪያ መርሃግብር በቂሊንጦ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ዛሬ መስከረም 27/2028 ዓ.ም ተካሄደ።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በስሩ ከሚያስተዳድራቸው 13 የኢንቨስትመንት ማዕከላት ውስጥ ቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን አንዱ ሲሆን በዞኑ ወደ ምርት ለመግባት በዝግጅት ላይ ካሉ ተቋማት አንዱ የሆነው የቅጥራን ማኑፋክቸሪንግ ሜዲካል ኢኪዮፕመንት ትሬዲንግ ፒኤልሲ ተመርቋል።
በመርሃግብሩ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬህይወት አበባ በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ምርቶች ጥራትና ፈዋሽናተቸው የተረጋገጡ እንዲሆኑ የተሰራው የምዘና እና ጥራት ቁጥጥር ሥራ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ማግኘቱ ከሀገር ውስጥ ባለፈ በመድኃኒት አቅርቦት ኢትዮጵያን የአፍሪካ ማዕከል ለማድረግ ለተጀመረው ሥራ መሠረት የሚጥል ስለመሆኑ ገልፀዋል።
የቅጥራን ማኒፋክቸሪንግ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አታኩሬ አያሌው ቅጥራን ከሀገራችንም አልፎ በሌሎች ሀገሮች ተወዳዳሪ በመሆን የውጭ ምንዛሬን ማስቀረት ዋነኛው አላማችን ነው ብለዋል።
ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት ከ150 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ ሲገባ ለ500 ሰዎች የስራ እድልን ይፈጥራል ተብሏል።




