0
#FastMereja I እናት ባንክ በዛሬዉ እለት ጥቅምት 1/2/2018 በአዲስ አበባ በፒያሳ አቡነ ጴጥሮስ ሀዉልት አካባቢ የቀድሞዉ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ህንፃ በልዩ ሁኔታ አስመርቋል።
ቅርንጫፉ ቀልጣፋ የባንክ አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ ሰዎች ስለ እናቶቻቸው የሚሰማችውን የሚጽፉበት መዝገብ የተዘጋጀለት እናቶች በቤት ውስጥ የሚገለገሉባቸው ባህላዊ ቁሳቁሶች ስለእናቶች የተጻፉ መጽህፍቶች የሚገኝበት እንደሆነ ተገልጿል።
እናት ባንክ ማህበራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር በአስኮ እካባቢ የሚገኘውን የህዝብ ቤተመጽሀፍት ከ3ዐ ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በመመደብ ደረጃውንና ጥራቱን በጠበቅ መልኩ አድሶ ለማስረከብ ዝግጁ ማድረጉን ተገልፀዋል።
ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስና ለሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ በማድረግ የበኩሉን ድረሻ እየተወጣ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በተጨማሪም የዜጎችን የፈጠራ ሥራ በመደገፍ ረገድ ሚናውን እየተወጣ የሚገኝ ሲሆን ፣የፈጠራ ባለቤት የሆኑ ወጣቶችን ሥራ ንድፈ ሀሳብ ወደ ተግባር በመቀየር በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በትብብር እየሰራ ይገኛል፡፡
#ቢዝነስ




