banner

5 ሚሊዮን ብር ወጪ የሆነበት የአፍሪካን አሊ የሙዚቃ አልበም ሊወጣ ነው ነው።

#FastMereja I ድምፃዊ አፍሪካን አሊ ሶስተኛው አልበሙን አጠናቆ ለአድማጮች ሊያድርስ መሆኑ ዛሬ ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።

አልበሙ “ታይሴ ዓዳ” የተሰኘው ሲሆን ከሌሎቹ የሙዚቃ አልበሞቹ ለየት የሚያደርገው የአፋር ህዝብን ቱባ ባህልን ለአለም የሚያስተዋወቅ መሆኑ እና በተለይ ለአዲሱ ትውልድ ባህሉን እንዲያውቅ ትልቅ አስተዋፀኦ ያለው ስራ መሆኑ ተነግሯል።

የአልበሙ መጠሪያ ታይሴ ዓዳ ትርጉሙ ድንቅ ባህል ማለት እንደሆነ ድምጻዊው ተናግሯል።

በአልበሙ በቅንብር፣ ሚክሲንግ እና ማስተሪንግ ስማገኘው ሳሙኤል (ዲታ ስቱዲዮ) ስድስት ትራኮችን የሰራ ሲሆን የቀሩትን 2 ትራኮች ደግሞ መክበብ ፀጋይ (ማርዮ) ሰርቷል።

ከታይሴ ዓዳ አልበም ዉስጥ አራት ትራኮች በቪድዮ ክሊፕ የተሰሩ ሲሆን እነዚህ ክሊፖችን ለመስራት የአፋር ቱሪስት መዳራሻዎች ድረስ በመሄድ ባህሉን በጠበቀ መልኩ ከፍተኛ ወጪ በማውጣት መሰራታቸው ተነግሯል።

በአጠቃላይ ይህ ኣልበም ለመሰራት ከአምስት ሚልዮን ብር በላይ ወጪ ወጥቶበት የተሰራ ሲሆን የዚህን ወጪ ሙሉ በሙሉ በድምፃዊ ኢንጅነር አፍሪካን ዓሊ ፕሮዲዩስ የተደረገ ነው፡፡

ታይሴ ዓዳ አልበም ስለ አፋር ቱባ ባህል፣ ስለ ሰላም፣ ስለ ፍቅር የሚዳስስ የሙዚቃ አልበም ነው። ጥቅምት 09/2018 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ይመረቃል።

አፍሪካን አሊ ሙዚቀኛ፣ ኢንጀነር እንዲሁም የዩነቨርሲቲ አስተማሪ ሲሆን አፍሪካን አሊ በትምህርቱ ዘርፍ በምህንደስና በሁለት ዘርፍ የማስተርስ ዲግሪ አለው።

#ኪነ_ጥበብ





4 comments

ፍቅር ያሸንፋል October 13, 2025 - 1:29 pm

ዘፈን ትታቹህ ቲክ ቶከር ብትሆኑ ገቢ አለው😎

Reply
ኢትዮ ቡታጅራ October 13, 2025 - 1:29 pm

አርቲስት ነው ለመሆኑ ከዚህ በፊት ዘፍኖ ያውቃል

Reply
ሳተ ናው October 13, 2025 - 1:30 pm

ቄሮች ግብር ልከፍሉበት ነዋ 😂😂😂😂

Reply
Ferhan Al Habesha Yirgalem October 13, 2025 - 1:31 pm

ጭራሽ ሶስተኛ አለበም?🤔🤔

Reply

Leave a Comment