banner

የፓኪስታንና አፍሪካ የንግድ ልማት ጉባኤና አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ተከፈተ

#FastMereja :- 5ኛው የፓኪስታንና አፍሪካ የንግድ ልማት ጉባኤ (PATDC) እና የፓኪስታን ምርቶች ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ በሚሊኒየም አዳራሽ ተከፈተ።

ከጥቅምት 6-8/2018 ዓ.ም የሚቆየው የሶስት ቀናት ኹነት በፓኪስታን እና በአፍሪካ መካከል የንግድና ኢንቨስትመንት አድሎችን ለመፍጠር የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

ጉባኤው የአፍሪካ እና የፓኪስታን ከፍተኛ የመንግስት ልዑካን፣ የንግድ መሪዎች፣ ባለሀብቶችና ባለሙያዎች የሚሳተፉበት ይሆናል።
በኤግዚቢሽኑ ላይ የፓኪስታን ኩባንያዎች የተለያዩ ምርቶቻቸውንና አገልግሎቶቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን ከነዚህም መካከል መድኃኒቶች፣ የህክምና መሣሪያዎች፣ አልባሳት፣ የምግብ ምርቶች፣ የውበት መጠበቂያዎች እና ሌሎችም እንደሚገኙበት ነዉ የተገለፀዉ።

በዝግጅቱም ላይ በንግድ ልማት ላይ ያተኮሩ የተለያዩ ዝግጅቶችን የሚያካትት ሲሆን ከእነዚህም መካከል የንግድ ጉባኤ፣ የሁለትዮሽ የንግድ ውይይቶች ፣ የመንግሥታት ውይይቶች እና የእራት ፕሮግራሞች እንደሚገኝበት ነዉ የተገለፀዉ።

የፓኪስታን ንግድ ሚኒስቴር እንደገለጸው፣ ይህ ጉባኤ በፓኪስታን እና በአፍሪካ መካከል የንግድ ግንኙነቶችን ለማጠናከር ትልቅ ሚና ይጫወታልም ብሏል።

#ኹነት





1 comment

Gebreselassie Desale October 16, 2025 - 12:44 pm

L9oihgfcxdooo9off

Reply

Leave a Comment