banner

የእናቶችና ህጻናት ህይወት ግድ ይለናል– ዶ/ር አንበሱ ቶላ የፈያ ኢንተግሬትድ ዴቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን መስራችና ዋና ዳይሬ

የእናቶችና ህጻናት ህይወት ግድ ይለናል– ዶ/ር አንበሱ ቶላ የፈያ ኢንተግሬትድ ዴቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን መስራችና ዋና ዳይሬክተር

በጅማ ዞን ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ 258 አባወራዎች(እማወራዎች) እና ከ 400 በላይ ለሆኑ ተማሪዎች ድጋፍ ተደረገ፡፡

ድጋፉን ያደረገው ፈያ ኢንተግሬትድ ዴቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን ነው፡፡

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ዘርፈ ብዙ ድጋፎችን እያደረገ የሚገኘው ሀገር በቀል የልማት ድርጅቱ በጅማ ዞን የምግብ ቁሳቁስና የደንብ ልብስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

በ2017 ዓ.ም ብቻ ከ 9 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ ከ 700 በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረጉንና ከ500 በላይ ለሆኑ ተማሪዎች የደብተርና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን የፈያ ኢንተግሬትድ ዴቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን መስራችና ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አንበሱ ቶላ ተናግረዋል፡፡

ድጋፉ የተደረገው ከአሜሪካ ስቴት ድፓርትመንት ፎሪን አሲስታንስ በኢሽዶ በኩል በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ መሆኑን ያሳወቁት ዋና ዳይሬክተሩ የልማት ድርጅቱ የሚሰራቸው የበጎ አድራጎት ስራዎች የዜጎችን ህይወት መቀየርን ታሳቢ ያደረጉ ናቸው ፤ ከምንም ነገር በላይ የእናቶችና ህጻናት ህይወት ግድ ይለናል ብለዋል፡፡

የበጎ አድራጎቱ ተጠቃሚዎችም ተቋሙ ከዚህ ቀደምም መሰል ድጋፎችን ሲያደርግላቸው መቆየቱን አንስተው ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

በድጋፍ መርሃ ግብሩ ላይ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት፣ ሥራ ስምሪትና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን ቢራቱን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ፈያ ኢንተግሬትድ ባለፉት 24 ዓመታት በርካታ ስራዎችን ያከናወነ ሀገር በቀል የልማት ድርጅት ሲሆን በእነዚህ ስራዎችም በርካታ ተፈናቃዮች ወደ መደበኛ ሕይወታቸው እንዲመለሱ እንዲሁም የዜጎች ህይወት እንዲቀየር አስተዋጽኦ አድርጓል

#FastMereja





Leave a Comment