banner

የፓስተር ቤኒሂን ክሩሴድ ፕሮግራም መጋቢት 18 በመስቀል አደባባይ ተዘጋጀ

#FastMereja I ፓስተር ቤኒሂን ከአንድ ቢሊዮን በላይ ሰዎችን በወንጌል የደረሰ፤ ከሰላሳ በላይ መጻህፍትን ያበረከተ፤ ላለፉት 50 ዓመታት ከ190 ሀገራት በላይ በመዘዋር በማገልገል ላይ ያለ አገልጋይ ሲሆን አሁን ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ለማገልገል በዝግጅት ላይ መሆኑ አስመልክቶ ዛሬጥቅምት 22 ቀን /2018 ዓ/ም በስካይ ላይት ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።

በመግለጫውም ፓስተር ቤኒሂን በመጋቢት ወር ለሶስት ቀናት በኢትዮጵያ በመገኝተ እንደሚያገለግሉ በአገልግሎታቸውም የአገልጋዮች ስልጠና እና የሁለት ቀን ክሩሴድ እንደሚኖር ተገልጿል።

የፓስተር ቤኒሂን የአፍሪካ ተጠሪ ፓስተር ሮበርት ካያንጃን ጨምሮ የአብያተክርስቲያን መሪዎች፣ አባቶችና አገልጋዮች የተገኙ ሲሆን በመግለጫቸውም ይህ ፕሮግራም የወንጌል አማኞች የጋራ ፕሮግራም ነው ስለዚህ ሁላችንም የወንጌል አማኞች ለዚህ ፕርግራም እየጸለይን እንድንቆይ፣ እንዲሁም የቤተክርስቲያን መሪዎችና አገልጋዮች ይህ የጋራ ፕሮግራማችን ነውና በጋራ እንድንሰራ ይሁን በማለት ጥሪ አስተላልፈዋል።

ይህን ክሩሴድ የሚያዘጋጀው Apex Events ሲሆን ፣በዚህ ፕሮገራም ላይ በጋራ ለመስራት ለሚፈልጉ ቤተክርስቲያናት በሙሉ ክፍት እንደሆነ ተገልጿል።





Leave a Comment