banner

ከ3000 በላይ የናሙና ምርመራዎችን ማድረግ የሚችለዉ ላብራቶሪ በይፋ ተከፈተ

#FastMereja I የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች (ዱባይ) ሀገር ተመዝግቦ የሚገኘውንና ዓለም አቀፍ የንግድ ምልክት የሆነው “ሜድሶል አድቫንስድ ሜዲካል ላብራቶሪ ” በዛሬው ዕለት ጥቅምት 22/2018ዓ.ም በኢትዮጵያ በይፋ ሥራ ጀምሯል፡፡

ከተመሰረተ 40 ዓመታት ያስቆጠረዉ ሜድሶል አድቫንስድ ሜዲካል ላብራቶሪ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱ በተለያዩ ምክንያቶች በሃገር ውስጥ ሊስሩ የማይችሉ እና ከፍተኛ ቴክኖሎጂን የሚጠይቁ ናሙናዎችን ከሃገር ውስጥ ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬቶች (ዱባይ) በመላክና በማሰራት ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የምርመራ ውጤቶች ለህብረተሰቡ እንዲሁም ለተለያዩ የህክምና ተቋማት ማድረስ እንደሆነ የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሱራፌል ሸዋ ገልፀዋል።

ከ3 ሺህ በላይ የናሙና ምርመራዎችን ማድረግ እንደሚችል የተገለፀዉ ይህ ላብራቶሪ በዘርፉ በተሰማሩ ባለድርሻ አካላት ወደ ሃገራችን ኢትዮጵያ በማስመጣት ለህክምና ላብራቶሪ ፍላጎት ዓይነተኛ አማራጭ መሆኑን ተገልጿል።

የጤና ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትና የግሉ የጤና ዘርፍ ጋር በመተባበር ማዕከሉን ወደ ሀገር ውስጥ በማስመጣት፤ በአፍሪካ የመጀመሪያውን የሜድሶል ቼን ማስጀመራቸው ነው የተገለጸው፡፡

#ጤና





Leave a Comment