0
#FastMereja I ተከሳሹ ወጣት ታርኩ አብርሃም ዕድሜ 22 የሆነ ግለሰብ በቀን ነሀሴ 12/2017 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 12:00 በሚሆንበት ጊዜ የጥላቻ ንግግር እና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁጥር 1185/2012 አንቀፅ 4ትን ተላልፈው ተከሳሽ በማህበራዊ ሚዲያ በመጠቀም የጌዴእ ብሄርን በቀጥታ ስሙን በማጥራት በጥላቻ ንግግር የተሳደበ በመሆኑ የገደብ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት መረጃውን ሲከታተል ቆይቶ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ አስተላልፏል።
በዐቃቤ ህግ ክስ ተመስርተው ፍርድ ቤቱም ሲያከራክር ቆይተው በቀን ህዳር 08/2018 ዓ.ም ላይ በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሻሽን ያርመዋል ለሎችንም ያስተምራል በማለት በ2 አመት ከ3 ወር ቀላል እስራት እንድቀጣ የገደብ ወረዳ ፍርድ ቤት ወስኗል።
ዘገባ፦ የገደብ ወረዳ ፖሊስ ህዝብ ግኑኝነት ነዉ
