0
#FastMereja I የዲጅታል ክፍያ መተግበሪያ የሆነው አሪፍ ፔይ ፋይናሻል ቴክኖሎጂ ዛሬ ሕዳር 09/2018 ዓ.ም በሐያት ሪጀንሲ ሆቴል ከቪዛ እና ከአቭሪኮም ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት ፈጸሙ።
አሪፍ ፔይ ከዓለም አቀፉ የክፍያ መፈጸሚያ ቪዛ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ከአቪኮም የተረከባቸውን 10ሺህ ዘመናዊ ፖስ ማሽኖች የዲጂታል ክፍያ አገልግሎትን በኢትዮጵያ ይዘርጋል።
ኢትዮጵያ የምትከተለውን የዲጅታል ኢኮኖሚ የሚደግፈው በአሪፍ ፔይ የበለጸገው አሪፍሾፕ የኦንላይን የገበያ መድረክ የጥሬ ገንዘብ ዝውውርን በማስቀረት የድጅታል ክፍያ አማራጭ ይዞ የመጣ ሲሆን ማንኛውም ሰው ካለበት ሆኖ በኦንላይን እቃን በመግዛት እዛው በድጅታል መንገድ መክፈል ይችላል ተብሏል።
አሪፍፔይ ነጋዴዎችን ከገንዘብ ብቻ ከሚደረጉ ስራዎች ወደ ዘመናዊ እና እርስ በርስ ሊተሳሰር የሚችል ዲጂታል ስነ-ምህዳር በመቀየር የኢትዮጵያን ዲጂታል ኢኮኖሚ ለማፋጠን ያለውን ተልዕኮ በቀጥታ ይደግፋል ተብላል።




