0
#FastMereja I የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ከሰላም ፀጥታ ፅ/ቤት እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ በጋራ በመሆን ባደረገዉ ድንገተኛ ኦኘሬሽን በሾላ ገበያ ህገወጥ የዶሮ እርድ ሲያከናዉኑ በነበሩ ግለሰቦች ላይ እርምጃ ወስዷል።
በተደረገው ክትትልና የተቀናጀ ኦፕሬሽን ግለሰቦቹ የሞቱ ዶሮዎችን በማረድ እና በማሸግ ለተለያዩ ሱቆችና ሆቴሎች ለማከፋፈል ሲዘጋጁ በነበረበት ሁኔታ የተያዙ ሲሆን በዚህም የታሸገ ዶሮ በቁጥር መቶ (100) ተበልቶ ለመታሸግ የተዘጋጀ አርባ ሁለት (42) ተይዟል።
የሞቱ ዶሮዎችን ለህብረተሰቡ እና ለሆቴሎች ከመከፋፈላቸዉ በፊት እርምጃ መወሰዱን የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ደንብ ማስከር ጽ/ቤት አስታውቋል ።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።




8 comments
አይድሌ ባለፈዉ የቀላሁት የሞተ ሳይሆን አይቀርም
ሳይሞቱ ይበላሉ እንዴ ታድያ ስራ አቀለሉ እንጂ
ይቺ የዉሸት አለም😂
Abesha yihen Hulu kifat kemin temare gin egzio
😭😭
በጣም ያሳዝናል ምግብ ገዝተን እንዳንበላ እያደረጉ ነው
አዘንኩ ለአ.አ ሕዝብ
በ ጠብቆ ይነበብ … ተወዛገብን ኮ ጎበዝ