#FastMereja I አርትስ ፕላስ የፊልም መተግበሪያ ኘላትፎርም አራት ፊልሞችን እና ሁለት ዘጋቢ ፊልሞችን ለስርጭት ለማብቃት ከፊልም አዘጋጆቹ ጋር በዛሬዉ እለት ህዳር 12/2018ዓ.ም የውል ስምምነት ፈፅመዋል።
በአርትስ ፕላስ የሚተላለፉት ፊልሞች በዛሬዉ የፊርማ ስነ- ስርአት ወቅት የፊልሞቹ ማስታወቂያዎች ለእይታ በቅተዋል::
በዚህ የፊልም መተግበሪያ ኘላትፎርም የሚተላለፉት ፊልሞች የፍቅር ጨዋታ፣ 11:59፣ እንግዱ እና አለሁ ሲሆኑ ጉጂ እና አክሱም የተሰኙ ሁለት ዘጋቢ ፊልሞችም ተካቷል።
አርትስ ፕላስ በርካታ ፊልሞችን ተከታታይ ድራማዎችን ዘጋቢ ፊልሞችን ቴአትሮችን ሌሎችንም አዝናኝ ይዘት ያላቸዉን ድራማዎች ይዞ እንደሚመጣ የአርትስ ቴሌቪዥን COO አቶ ራፋቱኤል ወርቁ ገልፀዋል።
የአሪፍፔይ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ረድኤት ፀጋብርሃን በበኩላቸዉ አርትስ ፕላስ ዓለምአቀፍ ከሆኑ የፊልም መተግበሪያዎች ጋር ተፎካካሪ መሆን እንደሚችል በመግለፅ ይህ መተግበሪያ አዳዲስ ደራሲያንን የፊልም ባለሙያዎች በእጅጉ የሚያበረታታ ፕላትፎርም መሆኑን በመግለፅ ሁሉም የፊልም ባለሙያዎች የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከአርትስ ፕላስ ጋር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል::
አርትስ ፕላስ በኢትዮጵያ በአይነቱ የመጀመርያው የዲጂታል ፕላትፎርም መድረክ በሀገሪቷ የፈጠራ ኢንዱስትሪ ውስጥ ትልቅ ፈጠራ ያለው ከአለም አቀፍ ደረጃዎች ጋር የተገነባ እና እንከን በሌለው ድረ-ገጽ እና የሞባይል አፕ ተደራሽ የሚሆን ነው፡፡




