0
#FastMereja I የኢትዮጵያ ምግብ መሃንዲሶች ማኅበር የአንደኛ አመት የምስረታ መርሐግብር ዛሬ ህዳር 20 ቀን 2018 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል ተካሄደ።
በመክፈቻ አውደ ጥናት ላይ ማህበሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ በምግብና ምግብ ዙሪያ የሚሰሩ ባለሞያዎችና ባለድርሻ አካላትን በአንድ ማገናኘት እንደሆነ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ምግብ መሐንዲሶች ማህበር በአገር አቀፍ ደረጃ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ የሚሳተፍ ሲሆን ከእነዚህም ጉዳዮች መካከል የምግብ ደህንነት እና ጥራት ማረጋገጥ ፣የተመጣጠነ ምግብ እና የህዝብ ግንዛቤ ፣የምግብ ዋስትና ፣ምርምር እና ልማትና እንዲሁም በሌሎችም ምግብ ነክ ጉዳዮች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰራም ተገልጿል።
በተጨማሪም ማኅበሩ ከአካዳሚክ ተቋማት (ዩኒቨርሲቲዎች እና ቴክኒካል ኮሌጆች) የመንግስት ኤጀንሲዎች የኢንዱስትሪ ባለድርሻ አካላት (የምግብ ማቀነባበሪያ ኩባንያዎች)፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ የምርምር ተቋማት እና የዘርፍ ማኀበራት ጋር በአጋርነት እንደሚሰራም አስታውቋል።
በዚህ ዓመት የማኀበሩ ትልቅ እቅድ በምግብና ምግብ ዙሪያ የሚሰሩ ኢንዱስትሪዎችን ማገዝ እንደሆነ ተነግሯል።




