#FastMereja I በሀገራችን ኢትዮጵያ ዝነኛ ት/ቤት ከሆኑት መካከል በአርሲ ዞን አርሲ ሮቤ የሚገኘው ዲደዓ ሁለተኛ ደረጃ በርካታ ተማሪዎችን አፍርቷል። በዚህ ት/ቤት የተማሩ በርካታ ተማሪዎች በሀገር ውስጥ እና በባህር ማዶ በስራ ላይ ይገኛሉ። ተማሪዎች ከማይረሷቸው መምህራን መካከል የታሪክ መምህሩ አላሮ ቲቶ ተጠቃሽ ናቸው። መምህር አላሮ እጅግ ጎበዝ መምህር ነው፡፡ ማየት የተሳነው ቢሆንም ለሰው ልጅ አእምሮ እንጂ አይን ብዙም መሰረታዊ እንዳልሆነ ህያው ምስክር ነው፡፡
የቀድሞ ተማሪያቸው ፍቄ ረታ ስለ መምህሩ እንደዚህ ብሏል “መምህር አላሮ አይነስውር ቢሆንም ከቤቱ ተነስቶ በእግሩ እስከ ዲደአ ትምህርት ቤት ይሄዳል፤ በተጨማሪም በክፍለጊዜው ከአንዱ ክፍል ወደሌላው ክፍል ያለምንም ረዳት መንቀሳቀስ መቻሉና ክፍል ውስጥ በሚያስተምርበት ወቅት ረባሽ ተማሪዎችን ለይቶ ማወቁ ሁሌም የሚገርመኝና የማደንቀው ነው፡፡
በተጨማሪም አላሮ የሚያስተምረውን የታሪክ ትምህርት በጥልቀት ስለሚያውቅ ለተማሪዎቹ ትልቅ መምህር ነው፡፡ እንደ አላሮ ባሉ መምህራን መማር እጅግ መታደል ነው፡፡” ነው ተብሎ ነበር።
ዛሬ ለፋስት መረጃ የደረሰው መልዕክት መምህር አላሮ ቲቶህይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል።

4 comments
ነፍስ ይማር 😥
RIP
RiP
Rip