banner

ሰክሰስ ፕላስ 50 ዊልቸሮችን ለአካል ጉዳተኞች በአዳማ አበረከተ

#FastMereja I ሰክሰስ ፕላስ የበጎ አድራጎት ድርጅት ዛሬ ሕዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በመገኘት ለሃምሳ አካል ጉዳተኞች የዊልቸር ድጋፍ አድርጓል።

የኦሮሚያ ክልል የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ አራርሶ ቢቂላ፣ የአዳማ ከተማ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በሪሶ ዶሪ፣ የሰክሰስ ፕላስ በጎ አድራጎት ድርጅት መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍሬው መንገሻ በተገኙበት ተበርክቷል።

የሰክሰስ ፕላስ በጎ አድራጎት ድርጅት የዊልቸር ድጋፉ በየሶስት ወሩ እየተደረገ ያለው ድጋፍ በተለያዩ አከባቢ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የተገለጸ ሲሆን ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ እና በትግራይ ክልል ድጋፉ ተከናውኗል።





Leave a Comment