#FastMereja I በሀገራችን የሎተሪ ሽልማት ታሪክ ትልቁና በዲጂታል ብቻ ገበያ ላይ የዋለው የ60 ሚሊዮን ብር ሎተሪ ዕጣ ሊወጣ 30 ቀናት እንደቀረዉ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት እና ታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽንስ በጋራ በዛሬው እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ህብረተሰቡ ከአሁን በፊት በወረቀት ከሚያውቃቸውን ሎተሪዎች በተጨማሪ አዳዲስ የሎተሪ አይነቶችን በመጨመር ለገበያ እያቀረብ ሲሆን ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ ደግሞ በኢትዮጵያ የሎተሪ ታሪክ ከፍተኛው ሽልማት የሆነውና ለመጀመሪያ ጊዜ በዲጂታል መንገድ ብቻ የቀረበውን የ60 ሚሊዮን ብር ሎተሪ ዕጣ ሊወጣ 30 ቀናት ብቻ መቅረቱ ተገለፀ፡፡
የ60 ሚሊዮን ብር ሎተሪ እድሜያቸው ከ18 አመት በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በየትኛውም አይነት ስልክ መቁረጥ እንደሚችሉም ተነግሯል።
የ60 ሚሊዮን ብር ሎተሪ ከጠቅላላ ሽያጭ ላይ ከ125 ሚሊዮን ብር በላይ ወይንም ከግማሽ በላይ ትኬቶች ለዕድለኞች ሽልማት የሚውሉ ሲሆን ከአጠቃላይ ሽያጩ ለሽልማት የሚወጣው የገንዘብ መጠን ወደ 53 በመቶ ማደጉ ነዉ የተገለፀዉ።
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ሎተሪው ገበያ ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ዋናውና ትልቁ ሽልማት እስከሚወጣበት ጥር 9 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የተለያዩ እድለኞች የተሸለሙ ሲሆን እስካሁንም ከ1200 በላይ እድለኞች በገንዘብና በአይነት የተለያዩ ሽልማቶችን ማሸነፍ ችለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በዝግጅቱ ላይ አሁን በዲጂታል መንገድ ገበያ ላይ ስለሚገኘው እለታዊ ሎተሪ የተነሳ ሲሆን አቶ ቴዎድሮስ እለታዊ ሎተሪ በዲጂታል መንገድ በ5 ብር ብቻ ከላይ በጠቀሷቸው መንገዶች ሁሉ የሚገኝ ሎተሪ መሆኑን ገልፀው በየ24 ሠአቱ እንደሚወጠና እድለኞችም እስከ 25,ዐዐዐ ብር እንደሚያሸንፉ ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በ1954 ለመጀመሪያ ጊዜ እድለኞችን ሲሸልም በ50,000 ብር የጀመረ ሲሆን በዚህ አመት ሽልማቱን አሳድጎ የአንደኛውን ዕጣ ሽልማት 60 ሚሊዮን ብር አድርሷል፤ ይሄም በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የሚኖረውን አስተዋጽኦ ከፍ ያደርገዋል።
ከዚህ በተጨማሪ የተቋሙ ድረ ገጽ ከተዋወቀበት ጊዜ ጀምሮ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የዲጂታል ቤተሠብ የሆኑ ሲሆን ይሄም በአጭር ጊዜ የተገኘ ትልቅ ስኬት ነው ።
በዛሬው እለትም በዲጅታል በቆረጠችው ትኬት አሸናፊ የሆነችው የመቂ ከተማ ነዋሪ ወ/ሮ ስምረት ኢቲቻ ህዳር 1 ቀን 2018 ዓም የወጣው የልዩ እድል ሎተሪ የአንደኛ ዕጣ 10 ሚሊየን ብር ሽልማቷን ተረክባለች።
በመጨረሻም ይሄ የዲጂታል ሎተሪ እንዲሳካ በአጋርነት አብረውን እየሠሩ ያሉትን የኢትዮ ቴሌኮም ቴሌ ብር አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ አዋሽ ባንክ፣ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ፣ ዳሽን ባንክ፣ አቢሲኒያ ባንክ፣ ዘረጋው ክላውድ አገልግሎት፣ ኤዲሲ ሪሰርችና ዴቨሎፕመንት እንዲሁም ሌሎች አጋሮች የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት እና ታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽንስ አመስግነዋል።
#ቢዝነስ ዘገባ





2 comments
betting ቤት ክፈቱልንና መጀመሪያ……ካልሆነ አትድከሙ አንገዛም
ጎሰቤቴ ነች ሔዳለሁ🙄